በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

መቅድም

መቅድም

አምላክ አፍቃሪ አባት ነው። 1 ጴጥሮስ 5:6, 7

አምላክ ፈጣሪያችን ከመሆኑም ሌላ ያስብልናል። አንድ ጥበበኛና አፍቃሪ አባት ልጆቹን እንደሚያስተምር ሁሉ አምላክም በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ከሁሉ በተሻለ መንገድ እንዴት መምራት እንደሚችሉ ያስተምራቸዋል።

አምላክ እንድንደሰትና ብሩህ ተስፋ እንዲኖረን የሚያደርጉ ውድ እውነቶችን ገልጦልናል።

አምላክን የምትሰማ ከሆነ የሚመራህና የሚጠብቅህ ከመሆኑም ሌላ የሚያጋጥሙህን ችግሮች እንድትቋቋም ይረዳሃል።

ከዚህም በላይ አምላክን የምትሰማ ከሆነ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ!

 አምላክ ‘ወደ እኔ ኑ። አዳምጡ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ’ ብሎናል። ኢሳይያስ 55:3