በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 ክፍል 14

ለይሖዋ ታማኝ መሆንህን ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ለይሖዋ ታማኝ መሆንህን ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ጎን ቁም። 1 ጴጥሮስ 5:6-9

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ከሚቃረኑ ማንኛውም ዓይነት ልማዶች ራቅ። ይህን ማድረግ ድፍረት ይጠይቃል።

በብሔራት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ምንም ዓይነት ተሳትፎ አታድርግ፤ እነሱ ይሖዋንም ሆነ መንግሥቱን አይደግፉም።

 አምላክን በመስማት ትክክለኛውን ምርጫ አድርግ። ማቴዎስ 7:24, 25

ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ወዳጅነት መሥርት፤ እነሱም ወደ አምላክ እንድትቀርብ ይረዱሃል።

ስለ አምላክ መማርህንና ትእዛዛቱን ለማክበር ጥረት ማድረግህን ቀጥል።

እምነትህ እየጠነከረ ሲሄድ ሕይወትህን ለይሖዋ ወስነህ መጠመቅ ይኖርብሃል።—ማቴዎስ 28:19

አምላክን ስማ። መጽሐፍ ቅዱስን አንብብ፤ የምታነበውንም መረዳት እንድትችል ይረዱህ ዘንድ የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቃቸው። ከዚያም የተማርከውን በሥራ ላይ አውል። እንዲህ የምታደርግ ከሆነ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ። —መዝሙር 37:29