በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ልጆቻችሁን አስተምሩ

 ትምህርት 14

መላዋን ምድር የሚገዛ መንግሥት

መላዋን ምድር የሚገዛ መንግሥት

ይህ መንግሥት የትኛው እንደሆነ መገመት ትችላለህ?— አዎ፣ የአምላክ መንግሥት ነው፤ ይህ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋታል። ስለዚህ መንግሥት ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?—

እያንዳንዱ መንግሥት መሪ ወይም ንጉሥ አለው። ንጉሡ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ያስተዳድራል። የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ማን እንደሆነ ታውቃለህ?— ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የሚኖረው በሰማይ ሲሆን በቅርቡ በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ ይነግሣል። ኢየሱስ በመላዋ ምድር ላይ ሲነግሥ ደስተኛ የምንሆን ይመስልሃል?—

በገነት ውስጥ ለማግኘት የምትጓጓው ነገር ምንድን ነው?

በጣም ደስተኞች እንደምንሆን የታወቀ ነው! በገነት ውስጥ ሰዎች እርስ በርስ አይጣሉም፤ ጦርነትም አይኖርም። ሁሉም ሰው እርስ በርስ ይዋደዳል። የሚታመም ወይም የሚሞት ሰው አይኖርም። ማየት የተሳናቸው ሰዎች ያያሉ፣ መስማት የማይችሉ ሰዎች ጆሮ ይከፈታል እንዲሁም አንካሳው መሮጥና መዝለል ይችላል። ሁሉም ሰው በቂ ምግብ ያገኛል። እንስሳት እርስ በርሳቸውም ሆነ ከእኛ ጋር በሰላም ይኖራሉ። የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ። በዚህ ብሮሹር ላይ ታሪካቸውን የተማርካቸው ብዙዎቹ ሰዎች ለምሳሌ ርብቃ፣ ረዓብ፣ ዳዊትና ኤልያስ ከሞት ይነሳሉ! እነዚህ ሰዎች ከሞት ሲነሱ ልታገኛቸው ትፈልጋለህ?—

 ይሖዋ ይወድሃል እንዲሁም ደስተኛ እንድትሆን ይፈልጋል። ስለ ይሖዋ መማርህንና እሱን መታዘዝህን ከቀጠልክ ውብ በሆነች ገነት ውስጥ ለዘላለም መኖር ትችላለህ! እንዲህ ዓይነት ሕይወት ማግኘት አትፈልግም?