በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አዲሱ የደቡብ አፍሪካ ምልክት ቋንቋ የርቀት የትርጉም ቢሮ

ሚያዝያ 29, 2022
ደቡብ አፍሪካ

የአካባቢ ንድፍና ግንባታ የደቡብ አፍሪካ ምልክት ቋንቋን የርቀት የትርጉም ቢሮ እድሳት አከናወነ

የአካባቢ ንድፍና ግንባታ የደቡብ አፍሪካ ምልክት ቋንቋን የርቀት የትርጉም ቢሮ እድሳት አከናወነ

የደቡብ አፍሪካ የአካባቢ ንድፍና ግንባታ ክፍል፣ ደርባን ውስጥ ለደቡብ አፍሪካ ምልክት ቋንቋ የርቀት የትርጉም ቢሮ ሆኖ የሚያገለግል ሕንፃ እድሳት በቅርቡ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። ቅርንጫፍ ቢሮው ሕንፃውን የገዛው መጋቢት 2020 ነበር፤ ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ በአቅራቢያው የሚገኙ አፓርታማዎችን ገዛ። ተርጓሚዎቹ ግንቦት 2022 ወደ አፓርታማዎቹ መግባት ይጀምራሉ።

የርቀት የትርጉም ቢሮው 17 ቤቴላውያንና በሳምንት የተወሰኑ ቀናት የሚሠሩ 25 የርቀት ሠራተኞች አሉት። ይህ ሕንፃ ያለበት ቦታ በደቡብ አፍሪካ ላሉት 283 መስማት የተሳናቸውና መስማት የሚቸግራቸው አስፋፊዎች እንዲሁም በአገሪቱ ለሚኖሩ 450,000 ገደማ መስማት የተሳናቸውና መስማት የሚቸግራቸው ሰዎች ጥራት ያለው ትርጉም ለማቅረብ የሚያመች ነው። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አብዛኞቹ መስማት የተሳናቸውና መስማት የሚቸግራቸው ሰዎች የሚኖሩት በክዋዙሉ-ናታል ግዛት ነው። በግዛቱ ውስጥ ያለው ትልቁ ከተማ ደግሞ ደርባን ነው።

በደቡብ አፍሪካ ምልክት ቋንቋ ትርጉም ቡድን ውስጥ የሚያገለግለው ወንድም ሲቡሲሶ ሚዚዚ እንዲህ ብሏል፦ “አዲሱ ቢሮ በደቡብ አፍሪካ ያለውን የምልክት ቋንቋ መስክ እንደሚጠቅምና ጉባኤዎችን እንደሚያጠናክር እርግጠኞች ነን።”

በደቡብ አፍሪካ ምልክት ቋንቋ የትርጉም ሥራና በዚህ ፕሮጀክት የይሖዋ በረከት ስላልተለየን ከልብ እናመሰግነዋለን።—መዝሙር 127:1