በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞችና እህቶች የመታሰቢያውን በዓል አክብረዋል

ሚያዝያ 21, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ አከበሩ

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ አከበሩ

በቺሊ የሚኖሩ ወንድሞች ሰላም ሲባባሉ

ሚያዝያ 15, 2022 በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮችና እነሱ የጋበዟቸው እንግዶች የጌታ ራትን አክብረዋል። ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ይህ በዓል ከ2019 ወዲህ በአካል ሲከበር ይህ የመጀመሪያው ነው። በዚህ ዓመት በተከበረው በዓል ላይ በአካል መገኘት ያልቻሉ ሰዎች በኢንተርኔት አማካኝነት ፕሮግራሙን ተከታትለዋል።

የይሖዋ ምሥክሮች በዓመት ውስጥ ከሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ሁሉ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ ነው። ይህ ዓመታዊ ስብሰባ በኮቪድ-19 ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት የተካሄደው በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ነው። በ2021 በተከበረው የመታሰቢያ በዓል ላይ ከ21 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ተገኝተዋል።

አንዳንዶች በመታሰቢያው በዓል ላይ በአካል ሲገኙ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። ለምሳሌ በሄይቲ የምትኖረው ማርኬንሲያ ሬሚ ከተጠመቀች አንድ ዓመት ሆኗታል፤ እንዲህ ብላለች፦ “የመታሰቢያውን በዓል በስብሰባ አዳራሽ ማክበር በመቻሌ በጣም ደስተኛ ነኝ። ደስታዬን ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል። ምርጥ የሆነ ቤተሰብ አባል እንደሆንኩ ተሰምቶኛል።”

ይሖዋ በዚህ ዓመት የተከበረውን የመታሰቢያ በዓል ስለባረከው አመስጋኞች ነን። በይበልጥ ደግሞ ይሖዋ አምላክና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ላሳዩን ከሁሉ የላቀ ፍቅር እጅግ አመስጋኞች ነን።—ዮሐንስ 3:16

 

አርጀንቲና

ቦሊቪያ

ብራዚል

ካምቦዲያ

መካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ

ኩክ ደሴቶች (ራሮቶንጋ)

ኢኳዶር

ኢንዶኔዥያ

እስራኤል

ጃፓን

ካዛክስታን

ኮሶቮ

ሜክሲኮ

ፓራጓይ

ፔሩ

ፊሊፒንስ

ፖላንድ

ሩማንያ

ስፔን

ታይዋን

ዩክሬን

ዩናይትድ ስቴትስ

ቬኔዙዌላ