በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 7, 2021
ካምቦዲያ

አዲስ ዓለም ትርጉም በካምቦዲያኛ ወጣ

አዲስ ዓለም ትርጉም በካምቦዲያኛ ወጣ

ሚያዝያ 3, 2021 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በካምቦዲያኛ ወጣ። የጃፓን ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል * የሆነው ወንድም ኬንጂ ቺክቺ የታተመውና በኤሌክትሮኒክ ቅጂ የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስ መውጣቱን አብስሯል። ፕሮግራሙ አስቀድሞ የተቀረጸ ሲሆን በካምቦዲያ ውስጥ ለሚገኙ ጉባኤዎችና ቡድኖች በሙሉ ተላልፏል።

ካምቦዲያኛ 16 ሚሊዮን ገደማ በሚሆኑ ሰዎች ይነገራል። በካምቦዲያኛ መስክ የሚያገለግሉ ከ1,100 በላይ አስፋፊዎች አሉ።

የጃፓን ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ማሳሂሮ ሃራዳ እንዲህ ብሏል፦ “ይህ ትርጉም አንባቢዎች እንደ ፍቅር፣ ርኅራኄና ምሕረት ያሉትን የይሖዋን ግሩም ባሕርያት እንዲያስተውሉ እንደሚረዳቸው እንተማመናለን። እንዲሁም ቅን ልብ ያላቸው ተጨማሪ ካምቦዲያውያን ወደ ይሖዋ እንዲቀርቡና እሱን ለማወደስ እንዲነሳሱ ያደርጋቸዋል የሚል ተስፋ አለን።”

ስድስት ተርጓሚዎችን ያቀፈ ሁለት የትርጉም ቡድን ለአራት ዓመታት በዚህ ሥራ ተካፍሏል። አንዲት የትርጉም ቡድኑ አባል እንዲህ ብላለች፦ “አዲሱ መጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊ ቃላትን አይጠቀምም። የማነበው ነገር ወዲያው ልቤን ይነካዋል። መዝሙር 139:17 ስሜቴን ጥሩ አድርጎ ገልጾታል፦ ‘ሐሳቦችህ ለእኔ ምንኛ ውድ ናቸው!’”

ሌላ ተርጓሚ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦ “ወንድሞች አዲሱን መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነቡ ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንደሚቀርቡ እተማመናለሁ። ብቸኝነት ሲሰማቸው ይሖዋ እንደሚወዳቸው ያስታውሳቸዋል። አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ሲገቡ ያረጋጋቸዋል። በጭንቀት ሲዋጡ ሰላም ያገኛሉ። መከራ ሲደርስባቸው ያጽናናቸዋል።”

ይህ ትርጉም በርካታ ሰዎች ስለ ታላቁ ፈጣሪያቸው ስለ ይሖዋ እንዲያውቁ እንደሚረዳቸው እንዲሁም ለእሱ የሚገባውን ክብርና ውዳሴ እንዲሰጡት እንደሚያነሳሳቸው እርግጠኞች ነን።—ራእይ 4:11

^ አን.2 በካምቦዲያ ያለውን ሥራ የሚከታተለው የጃፓን ቅርንጫፍ ቢሮ ነው።