በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጋቢት 16, 2021
ኢኳቶሪያል ጊኒ

በኢኳቶሪያል ጊኒ የተከሰተው ከባድ ፍንዳታ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል

በኢኳቶሪያል ጊኒ የተከሰተው ከባድ ፍንዳታ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል

ቦታ

ኢኳቶሪያል ጊኒ ውስጥ በባታ ከተማ፣ ሞንዶንግ ኤንክዋንቶማ አካባቢ

የደረሰው አደጋ

 • መጋቢት 7, 2021 ኢኳቶሪያል ጊኒ ውስጥ ትልቅ በሆነው ከተማ በሚገኘው የጦር ካምፕ ፍንዳታዎች ተከስተው ነበር። እነዚህ ፍንዳታዎች ከፍተኛ ውድመት አስከትለዋል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

 • 12 አስፋፊዎች መጠነኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

 • 42 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

 • የአንዲት እህት የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሕይወቷ አደጋ ላይ ነው

 • አንዳንድ አስፋፊዎች የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ዘመዶቻቸውን በሞት አጥተዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

 • 23 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

 • 6 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

 • 6 ቤቶች ፈርሰዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

 • የእርዳታ ሥራውን የሚያስተባብር የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል፤ ኮሚቴው የደረሰውን ጉዳት መጠን ለማወቅና አስፈላጊውን እርዳታ ለመስጠት ከወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ከጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር ሆኖ እየሠራ ነው

 • በተጨማሪም የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ሽማግሌዎች አስፋፊዎችን እያጽናኑ ነው

 • የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

በዚህ አደጋ የተጠቁት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ይሖዋን መጠጊያቸው ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ እንጸልያለን።—መዝሙር 46:1