በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ባለአራት ፎቁ ሕንፃ እድሳቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚኖረውን መልክ የሚያሳይ ሥዕል

ሚያዝያ 25, 2022
አንጎላ

እድሳት የተደረገለት አንድ ሕንፃ የአንጎላን ቅርንጫፍ ቢሮ ለማስፋፋት ሊውል ነው

እድሳት የተደረገለት አንድ ሕንፃ የአንጎላን ቅርንጫፍ ቢሮ ለማስፋፋት ሊውል ነው

ለአንጎላ ቅርንጫፍ ቢሮ ተጨማሪ መኖሪያና ቢሮ እንዲሆን የታሰበው ባለአራት ፎቅ ሕንፃ የእድሳት ሥራው ሰኔ 2022 እንደሚጀምር ይጠበቃል። በአንጎላ ያሉት 207 የቤቴል ቤተሰብ አባላት በ2003 የተወሰነው የአሁኑ ቅርንጫፍ ቢሮ አልበቃቸውም።

በአሁኑ ወቅት አንዳንዶቹ የቤቴል ቤተሰብ አባላት የሚኖሩት በኪራይ ቤቶች ውስጥ ነው፤ በመሆኑም ተጨማሪ መኖሪያ ያስፈልጋል። ወንድሞች ሕንፃውን የገዙት ታኅሣሥ 2021 ነው። ሕንፃው የሚገኘው ከአሁኑ ቅርንጫፍ ቢሮ አቅራቢያ ነው።

እድሳት የተደረገለት ሕንፃ 57 የመኖሪያ ክፍሎችና 60 ቢሮዎች ይኖሩታል። የመኖሪያ ክፍሎቹ ለቢሮ የሚያገለግል ቦታ ይኖራቸዋል፤ ለቢሮ የሚያገለግለው ስፍራ ደግሞ ዝግ ቢሮዎችና ክፍት ቢሮዎች ይኖሩታል። ከዚህም ሌላ እድሳት የተደረገለት ሕንፃ የስብሰባ አዳራሽና እንደ አስፈላጊነቱ ለተለያየ ዓላማ ሊውሉ የሚችሉ ክፍሎች ይኖሩታል። ለቢሮ የሚያገለግለው ስፍራ እንደ አስፈላጊነቱ መነሳት፣ ተመልሶ መገጠም ወይም መስተካከል የሚችል ግድግዳ ይኖረዋል።

በአሁኑ ወቅት በኪራይ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩት የቤቴል ቤተሰብ አባላት የካቲት 2024 ወደ አዲሱ ሕንፃ እንደሚዛወሩ ይጠበቃል።

የአንጎላ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ሳሙኤል ካምፖስ እንዲህ ብሏል፦ “ቅርንጫፍ ቢሮውን ማስፋፋት እንዲቻል ስንጸልይ እንዲሁም ከዓለም አቀፉ ንድፍና ግንባታ ክፍል ጋር ተባብረን ስንሠራ ቆይተናል። ይህ ሕንፃ መገዛትና መታደስ መቻሉ የጸሎታችን መልስ ነው።”

አንጎላ ውስጥ ከ160,000 በላይ አስፋፊዎች አሉ። ባለፈው ዓመት ከ400,000 የሚበልጡ ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ ተገኝተዋል፤ በተጨማሪም አስፋፊዎች ከ200,000 የሚበልጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መርተዋል። የመንግሥቱን ጉዳዮች ለማስፋፋት የሚያስችለውን ይህን የቅርንጫፍ ቢሮ እድሳት ሥራ ይሖዋ እንደሚባርከው እርግጠኞች ነን።—1 ዜና መዋዕል 29:16