ግንቦት 3, 2022
ሩሲያ
ጸሎት ብርታት ሰጥቷቸዋል
በኡድሙርቲያን ሩፑብሊክ የሚገኘው የቮትኪንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የወንድም ሰርጌ ጎቦዜቭን እና የወንድም ሚካይል ፖታፖቭን ጉዳይ ተመልክቶ በቅርቡ ውሳኔውን ያሳውቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
የክሱ ሂደት
ጥር 20, 2021
ሰርጌ እና ሚካይል የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አደራጅተዋል በሚል የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው
ጥር 21, 2021
የሰርጌ አፓርታማ ተፈተሸ። ባለሥልጣናቱ የሰርጌን መንጃ ፈቃድ፣ የመኪና ሰነዶች፣ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች፣ የፎቶ አልበም እና የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ጨምሮ የተለያዩ የግል ንብረቶቹን ወረሱበት። ባለሥልጣናቱ ሚካይልን በቁጥጥር ሥር በማዋል ቤቱን ፈተሹ
ጥር 22, 2021
ሰርጌ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ። ሚካይል ወደ ማረፊያ ቤት ተወሰደ
ግንቦት 18, 2021
ሰርጌ ከቁም እስር ተፈታ፤ ሆኖም የጉዞ ገደብ ተጣለበት
ግንቦት 19, 2021
ሚካይል ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ ሆኖም የጉዞ ገደብ ተጣለበት
ጥቅምት 7, 2021
ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ሰርጌና ሚካይል በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና በጸሎት አማካኝነት እምነታቸውን ለማጠናከር ጥረት ሲያደርጉ ይሖዋ እነሱን መደገፉን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—ቆላስይስ 2:6, 7