ግንቦት 5, 2022
ሩሲያ
ይሖዋ ለሰርጌ ኩዝነትሶቭ ኃይል ሰጥቶታል
በካባረቭስክ ክልል የሚገኘው የቭያዜምስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የወንድም ሰርጌ ኩዝነትሶቭን ጉዳይ ተመልክቶ በቅርቡ ውሳኔውን ያሳውቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍ የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
የክሱ ሂደት
መስከረም 3, 2020
የፌዴራል ደህንነት አባላት የሰርጌን ቤት ፈተሹ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች፣ ፍላሽ ዲስኮችና ጽሑፎች ወረሱ
ሚያዝያ 2, 2021
በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ። የባንክ ሒሳቡ ታገደ
ኅዳር 9, 2021
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ለስሙ ሲሉ የሚደርስባቸውን ስደት በጽናት እየተቋቋሙ ላሉት በሩሲያና በክራይሚያ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ኃይል እንደሚሰጣቸው እርግጠኞች ነን።—ራእይ 2:3