በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 2, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት JW ላይብረሪ አፕሊኬሽንን አገደ

የሩሲያ ፍርድ ቤት JW ላይብረሪ አፕሊኬሽንን አገደ

መጋቢት 31, 2021 በሴንት ፒተርስበርግ የሚገኘው የኦክትያቢርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት JW ላይብረሪ አፕሊኬሽንን ጽንፈኛ ብሎ የፈረጀው ሲሆን በመላው ሩሲያ ፌዴሬሽንም ሆነ በክራይሚያ እንዲታገድ ወስኗል። ውሳኔው ወዲያውኑ ተግባራዊ ይሆናል። ተጠቃሚዎች አሁንም አፕሊኬሽኑን መጠቀም አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ወንድሞች ውሳኔውን አስመልክቶ ይግባኝ ይጠይቃሉ።