በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 1, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ታትያና ዛጉሊና ጥፋተኛ ነች በማለት የገደብ እስራት ፈረደባት

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ታትያና ዛጉሊና ጥፋተኛ ነች በማለት የገደብ እስራት ፈረደባት

መጋቢት 31, 2021 በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣን አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ታትያና ዛጉሊና ጥፋተኛ ናት የሚል ውሳኔ አስተላለፈ። እህት ታትያና የሁለት ዓመት ከስድስት ወር የገደብ እስር ተፈርዶባታል። እርግጥ አሁን ወህኒ አትወርድም።