በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጋቢት 8, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ሰርጌ ቨርክሆቱሮቭ ላይ የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ፈረደበት

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ሰርጌ ቨርክሆቱሮቭ ላይ የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ፈረደበት

በኒዥኒ ኖቭጎሮድ የሚገኘው የፕሪኦክስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ መጋቢት 5, 2021 ወንድም ሰርጌ ቨርክሆቱሮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አስተላልፏል። ወንድም ሰርጌ የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወኅኒ ቤት አይወርድም። ወንድም ሰርጌ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ታውቋል።