በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሐምሌ 26, 2019
ስፔን

ማድሪድ፣ ስፔን—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ማድሪድ፣ ስፔን—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከሐምሌ 19-21, 2019

  • ቦታ፦ በማድሪድ፣ ስፔን የሚገኘው ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ የስፔን ምልክት ቋንቋ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 52,516

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 434

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 6,300

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሃንጋሪ፣ ማዕከላዊ አሜሪካ፣ ስሎቬንያ፣ ቡልጋሪያ፣ ቱርክ፣ ታይዋን፣ ኔዘርላንድስ፣ አልባኒያ፣ አርጀንቲና፣ ካናዳ፣ ኮሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዶሚኒካን ሪፑብሊክ፣ ጋና፣ ፔሩ

  • ተሞክሮ፦ ልዑካኑ ካረፉባቸው ሆቴሎች የአንዱ ማኔጀር የሆነው ሴዛር ሎፔዝ እንዲህ ብሏል፦ “ያየነው ነገር በጣም አስደናቂ ነው። ሠራተኞቻችን በፕሮግራሙ ላይ ስለተገኙት ልዑካን ፈገግታ፣ መልካም ባሕርይና ወዳጃዊ ስሜት አውርተው ሊጠግቡ አልቻሉም። ልዑካኑ [“ፍቅር ለዘላለም ይኖራል” የሚለውን] መልዕክት እዚህ ከመምጣታቸው በፊትም የተማሩት ይመስላል። በሆቴላችን ያረፉ ልዑካን በሙሉ አፍቃሪ ነበሩ። ከዚህ በኋላም እንግዶቻችሁን ብንቀበል ደስ ይለናል።”

 

የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች በአዶልፎ ሱዋሬዝ ማድሪድ ባራሃስ አየር ማረፊያ ልዑካኑን በደስታ ሲቀበሉ

አንዲት የአካባቢው እህትና አንዲት ልዑክ ማድሪድ ውስጥ የስብሰባውን መጋበዣ በመጠቀም ሲሰብኩ

ልዑካኑ ለጠዋቱ ስብሰባ ወደ ስታዲየሙ ሲገቡ

ከተለያዩ አገራት የመጡ ልዑካን በዓርብ ዕለቱ ስብሰባ መደምደሚያ ላይ በፈገግታ እጃቸውን ሲያውለበልቡ

ስብሰባው በቀጥታ ከተላለፈባቸው ቦታዎች በአንዱ የተገኙ ሁለት ልጆች በስፓንኛ የወጣውን የተሻሻለውን አዲስ ዓለም ትርጉም ሞባይላቸው ላይ ሲያሳዩ። መጽሐፍ ቅዱሱ ዓርብ ዕለት በተደረገው ስብሰባ ላይ በማድሪድና ስፔን ውስጥ በሚገኙ ሌሎች 11 የስብሰባ ቦታዎች በተመሳሳይ ጊዜ ወጥቷል።

በስብሰባው ላይ ከተጠመቁት 434 ወንድሞችና እህቶች መካከል አንዱ በፈገግታ ከውኃው ሲወጣ

ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እሁድ ቀን በስብሰባው መደምደሚያ ላይ ሕዝቡን ሲሰናበቱ

በስብሰባው ወቅት ወንድሞችና እህቶች በደስታ ሲያጨበጭቡ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጌሪት ሎሽ ስብሰባው ካለቀ በኋላ ከልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮቹ አንዷን ሰላም ሲል

በቀለማት ያሸበረቀ ልብስ የለበሱ እህቶች ምሽት ላይ በተደረገው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ የስፔንን ባሕላዊ ውዝዋዜ ሲያሳዩ