ጥቅምት 6, 2025
ሩሲያ
እህት ናታሊያ ኖቮሴሌትስካያ
“ይሖዋ የሚወዳቸውን እንዳይንከባከብ የሚያግደው አንዳች ነገር የለም”
መስከረም 30, 2025 በክራስኖዳር ግዛት የሚገኘው የቭይሴልኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ናታሊያ ኖቮሴሌትስካያን ጥፋተኛ በማለት የሁለት ዓመት የገደብ እስራት በይኖባታል። አሁን ላይ እስር ቤት አትገባም።
አጭር መግለጫ
በእነዚህ አስቸጋሪ የመጨረሻ ቀናት ይሖዋ ‘አስተማማኝ መጠጊያና ጋሻ’ በመሆን ታማኝ ፍቅሩን እያሳየን በመሆኑ አመስጋኝ ነን፤ እስከ መጨረሻው እንደምንታመንበት ማሳየታችንን እንቀጥል።—መዝሙር 144:2

