አማርኛ
“የተስፋ መቁረጥ ዋናው ማርከሻ ጸሎት ነው”
https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/702026127/univ/art/702026127_univ_sqr_xl.jpg

ሐምሌ 1, 2026
ሩሲያ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ሮማን ኾሪኮቭ፣ ወንድም ዩሪ ኾሪኮቭ እና ወንድም ኪሪል ስዬቭዬሪንቺክ

“የተስፋ መቁረጥ ዋናው ማርከሻ ጸሎት ነው”

“የተስፋ መቁረጥ ዋናው ማርከሻ ጸሎት ነው”

ሰኔ 19, 2026 በኻንቲ ማንሲ (ዩግራ) ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የሱርጉት ከተማ ፍርድ ቤት፣ በሦስት ወንድሞች ላይ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሦስቱም የተበየነባቸው ቅጣት የገደብ እስራት ነው፤ ወንድም ሮማን ኾሪኮቭ ስድስት ዓመት ከአራት ወር፣ ወንድም ዩሪ ኾሪኮቭ ስድስት ዓመት ከስድስት ወር፣ ወንድም ኪሪል ስዬቭዬሪንቺክ ደግሞ አራት ዓመት ተፈርዶባቸዋል።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ሕዝቦቹ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለማሟላት ምንጊዜም በንቃት ይመለከታል፤ እነሱን ለማበርታትና ለመርዳት ሁሌም ዝግጁ ነው፤ ይህን ማሰባችን ያጽናናናል።—መዝሙር 121:3, 4