አማርኛ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ይግባኛቸው ከታየ በኋላ ታሰሩ | ይሖዋን ማገልገል ትልቅ መብት ነው
https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/702024081/univ/art/702024081_univ_sqr_xl.jpg

በስተ ግራ፦ ወንድም ዬቭጌኒ ስቴፋኒዲን። በስተ ቀኝ፦ ወንድም አሌክሳንደር ቮትያኮቭ

ሚያዝያ 23, 2024 | የታደሰው፦ የካቲት 7, 2025
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ይግባኛቸው ከታየ በኋላ ታሰሩ | ይሖዋን ማገልገል ትልቅ መብት ነው

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ይግባኛቸው ከታየ በኋላ ታሰሩ | ይሖዋን ማገልገል ትልቅ መብት ነው

የካቲት 4, 2025 የኡድሙርቲያን ሪፑብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዬቭጌኒ ስቴፋኒዲን እና ወንድም አሌክሳንደር ቮትያኮቭ ያቀረቡትን ይግባኝ ከተመለከተ በኋላ ቀደም ሲል የተበየነባቸውን ፍርድ ለውጦታል። ዬቭጌኒ የስድስት ዓመት፣ አሌክሳንደር ደግሞ የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ተበይኖባቸዋል። ወንድሞች ከችሎት ወዲያውኑ ወደ ወህኒ ተወስደዋል።

ጥቅምት 25, 2024 በኡድሙርቲያን ሪፑብሊክ፣ በኢዢፍስክ ከተማ የሚገኘው የፐርቮማይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዬቭጌኒ ስቴፋኒዲን እና ወንድም አሌክሳንደር ቮትያኮቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ዬቭጌኒ የስድስት ዓመት፣ አሌክሳንደር ደግሞ የስድስት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። አሁን ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

እንደ አሌክሳንደር እና ዬቭጌኒ ሁሉ እኛም በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ለይሖዋ ‘ያለፍርሃት ቅዱስ አገልግሎት ማቅረብ’ መቻል ትልቅ መብት እንደሆነ ይሰማናል።​—ሉቃስ 1:74, 75

የክሱ ሂደት

  1. ሚያዝያ 14, 2021

    የደህንነት ሰዎች የዬቭጌኒን ቤት ፈተሹ

  2. ታኅሣሥ 13, 2022

    አሌክሳንደር እና ዬቭጌኒ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  3. ታኅሣሥ 14, 2022

    ፖሊሶች የሁለቱንም ቤቶች ፈተሹ። አሌክሳንደር ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ። ዬቭጌኒ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  4. ታኅሣሥ 15, 2022

    አሌክሳንደር ከጣቢያ ተለቀቀ፤ የቁም እስረኛ ተደረገ

  5. ሰኔ 9, 2023

    አሌክሳንደር ከቁም እስር ተፈታ፤ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  6. ነሐሴ 17, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ