በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥቅምት 8, 2018
አዲስ ነገር

አዳዲስ ጽሑፎች እንዲሁም በድረ ገጾችና በአፕሊኬሽኖች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች

አዳዲስ ጽሑፎች እንዲሁም በድረ ገጾችና በአፕሊኬሽኖች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች

ዎች ታወር ባይብል ኤንድ ትራክት ሶሳይቲ ኦቭ ፔንስልቬንያ ጥቅምት 6, 2018 ባደረገው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ሁለት አዳዲስ ጽሑፎች ወጥተዋል። የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ! የተባለው መጽሐፍ በሕዝቅኤል ትንቢት ላይ የተመሠረተ ነው፤ ለማንበብና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ የተባለው ብሮሹር ደግሞ የይሖዋ ምሥክሮች የማንበብና የማስተማር ችሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ንጹሕ አምልኮ የተባለው መጽሐፍ በእንግሊዝኛ፣ ማስተማር የተባለው ብሮሹር ደግሞ በተለያዩ ቋንቋዎች jw.org ድረ ገጽ ላይም ሆነ JW ላይብረሪ አፕሊኬሽን ላይ ይገኛሉ። ንጹሕ አምልኮ የተባለው መጽሐፍ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በሌሎች ቋንቋዎችም ይወጣል።

በተጨማሪም የበላይ አካሉ በድረ ገጾቻችንና በአፕሊኬሽኖች ላይ ጉልህ ለውጥ እንዲደረግ ፈቃድ እንደሰጠ የሚገልጽ ማስታወቂያ በዓመታዊው ስብሰባው ላይ ተነግሯል። jw.org የተባለው ድረ ገጽ የJW ብሮድካስቲንግ እና የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት ዓይነት ይዘት እና ገጽታ እንዲኖረው ይደረጋል። ከዚህም ሌላ JW ላይብረሪ አፕሊኬሽንከዎችታወር ላይብረሪ (እንግሊዝኛ) ጋር ተመሳሳይ ይዘትና ገጽታዎች እንዲኖሩት ይደረጋል፤ አልፎ ተርፎም በአሁኑ ጊዜ በjw.org ድረ ገጽ ላይ ብቻ የሚገኙ ነገሮችንም ይዞ ይወጣል። የአዲሱ ድረ ገጽ እና አፕሊኬሽን አጠቃላይ ገጽታ አንድ ዓይነት ሲሆን ለአጠቃቀምም ይበልጥ ቀላል እንዲሆን ይደረጋል። ለምሳሌ ያህል፣ ማሻሻያ የተደረገባቸው ድረ ገጾች እና አፕሊኬሽኖች ለአጠቃቀም አስቸጋሪ እንዳይሆኑ ሲባል ዋና ዋና ገጽታዎቻቸው ቀለል ባለ መንገድ ተዘጋጅተዋል፤ ይህም ተጠቃሚዎቹ መንፈሳዊ ምግብ በፍጥነት እንዲያገኙ አስተዋጽኦ ያበረክታል። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት የእቅድና የዲዛይን ሥራ ተጀምሯል። በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ የተወሰኑትን ማሻሻያዎች ማግኘታችን አይቀርም።