በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 14, 2019
አዲስ ነገር

አዲስ ዓለም ትርጉም በአምስት ቋንቋዎች ወጣ

አዲስ ዓለም ትርጉም በአምስት ቋንቋዎች ወጣ

ጥር 12, 2019 በቤኒን ሲቲ፣ ናይጄርያ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በኢሶኮ ቋንቋ፣ የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በዮሩባ ቋንቋ መውጣቱ ተገለጸ። በዚያው ቀን በደድሊ፣ ዌስት ሚድላንድስ፣ እንግሊዝ ከአዲስ ዓለም ትርጉም ላይ የማቴዎስ መጽሐፍ በብሪታንያ ምልክት ቋንቋ መውጣቱ ተገለጸ።

አዲስ ዓለም ትርጉም ፊሊፒንስ ውስጥም በሁለት ቋንቋዎች ወጥቷል። ጥር 12, 2019 በላፑ ላፑ ሲቲ፣ ሴቡ የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በሴብዋኖ ቋንቋ መውጣቱ ተገለጸ። በቀጣዩ ቀን ደግሞ በፓሎ፣ ሌይቴ አዲስ ዓለም ትርጉም በዋራይ ዋራይ ቋንቋ መውጣቱ ተገለጸ። አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ ወይም በከፊል በ179 ቋንቋዎች ተተርጉሟል፤ ከእነዚህ መካከል በ2013 በወጣው እትም ላይ ተመሥርተው ተሻሽለው የወጡ 18 ቋንቋዎችም ይገኙበታል።