ከግራ ወደ ቀኝ፦ ኦሌግ ፖስትኒኮቭ፣ ቫለሪ ቶልማዞቭ፣ ማክሲም ባርባዝዩክ እና አሌክሳንደር ኮስትዩክ
በሩሲያ በድብቅ ካሜራ የተቀረጹ አራት ወንድሞች የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው
የሩሲያ መንግሥት አራት ወንድሞቻችን ላይ እስር በይኗል። ሦስት ወንድሞች ስድስት ዓመት የተፈረደባቸው ሲሆን አንድ ወንድም ደግሞ ስድስት ዓመት ከሁለት ወር ተፈርዶበታል። ለክሱ በዋነኝነት ማስረጃ ሆነው የቀረቡት የሩሲያ የደህንነት ሰዎች በድብቅ የቀርጿቸው ቪዲዮዎች ናቸው። በቪዲዮዎቹ ላይ ወንድሞችና እህቶች አንድ ላይ ተሰብስበው ሰላማዊ በሆነ መንገድ አምልኮ ሲያካሂዱ እንዲሁም በመደምደሚያው ጸሎት ላይ ይሖዋ የሚደርስባቸውን ስደት መቋቋም እንዲችሉ እንዲረዳቸው ሲጠይቁት ይታያል።
የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ፣ ሩሲያ ከ2017 አንስቶ በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የጣለችው እገዳ ከሕግ አንጻር ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ በተደጋጋሚ ቢገልጹም ወንድሞቻችን ወንጀለኛ ተብለው ተፈርዶባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ “ሩሲያ በድብቅ ካሜራ የቀረጸቻቸውን አራት የይሖዋ ምሥክሮች አሰረች” በሚል ርዕስ ሮይተርስ ያወጣውን የእንግሊዝኛ ዜና ለመመልከት ሊንኩን ተጫን።

