በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Thomas Jackson/​Stone via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

2024⁠ን በተስፋ መጀመር​—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

2024⁠ን በተስፋ መጀመር​—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ብዙዎች በ2024 በዓለም ላይ የተጋረጡት ችግሮች ምንም መፍትሔ እንዳላቸው አይሰማቸውም። ሆኖም ስለ ወደፊቱ ጊዜ አስተማማኝ ተስፋ ማግኘት እንችላለን። ከየት?

መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይሰጣል

 መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ ሕይወታችንን ተስፋ አስቆራጭ ያደረጉብንን ችግሮች በሙሉ አምላክ እንደሚያስወግድልን ተስፋ ይሰጣል። በቅርቡ አምላክ “እንባን ሁሉ [ከዓይናችን] ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”​—ራእይ 21:4

መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜም ሊረዳህ የሚችለው እንዴት ነው?

 መጽሐፍ ቅዱስ አሉታዊ ስሜቶችን ለማስወገድና አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ ሊረዱህ የሚችሉ ተስፋዎችን ይዟል። (ሮም 15:13) በተጨማሪም በውስጡ የሚገኙት ጠቃሚ ምክሮች በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሙህን እንደ ድህነት፣ የፍትሕ መጓደልና ሕመም ያሉ ችግሮች ለመወጣት ሊረዱህ ይችላሉ።

 አንተም ሆንክ ቤተሰብህ 2024 አስደሳች ዓመት እንዲሆንላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ የሚረዳህ እንዴት እንደሆነ ይበልጥ መማር ትፈልጋለህ? በግለሰብ ደረጃ የምንሰጠውን ከክፍያ ነፃ የሆነ አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለምን አትሞክረውም? አምላክ በአሁኑ ጊዜ “ሰላም” ወደፊት ደግሞ “የተሻለ ሕይወት” የሚሰጥህ እንዴት እንደሆነ ተማር።​—ኤርምያስ 29:11