በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከላይ በስተ ግራ፦ Marek M. Berezowski/Anadolu Agency via Getty Images፤ ከታች በስተ ግራ፦ Halfpoint Images/Moment via Getty Images፤ መካከል፦ Zhai Yujia/China News Service/VCG via Getty Images፤ ከላይ በስተ ቀኝ፦ Ismail Sen/Anadolu Agency via Getty Images፤ ከታች በስተ ቀኝ፦ E+/taseffski/via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

2023፦ የጭንቅ ዓመት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

2023፦ የጭንቅ ዓመት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በ2023 በዓለም ዙሪያ ያየናቸው ክስተቶች መጽሐፍ ቅዱስ “የመጨረሻዎቹ ቀናት” በማለት በሚጠራው ጊዜ ላይ እንደምንኖር የሚጠቁሙ የማያሻሙ ማስረጃዎች ናቸው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1) በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ያሉት ክንውኖች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዘመናችን አስቀድሞ ከተናገረው ነገር ጋር የሚስማሙት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች እና ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች

 “ጦርነትና የጦርነት ወሬ።”ማቴዎስ 24:6

  •   “በብዙ የዓለማችን ክፍሎች ጦርነት እየተስፋፋ ነው።” a

 “በተለያየ ስፍራ የምድር ነውጥ።”ማርቆስ 13:8

  •   “ከ2023 መጀመሪያ አንስቶ በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ ከ7 በላይ የተመዘገቡ 13 የምድር ነውጦች ተከስተዋል፤ ይህም እስካሁን ከተመዘገቡት ከፍተኛ ቁጥሮች መካከል አንዱ ነው።” b

 አውዳሚ ርዕደ መሬት ቱርክንና ሶርያን መታ” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

 “የሚያስፈሩ ነገሮች።”ሉቃስ 21:11

  •   “አሁን ላይ ምድራችን ከመሞቅ አልፋ ነዳለች።”—የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ c

 “የምግብ እጥረት።”ማቴዎስ 24:7

  •   “2023፦ ቤተሰባቸውን ለመመገብ ደፋ ቀና ለሚሉ ቤተሰቦች እጅግ ፈታኝ የነበረ ሌላ ዓመት።” d

 “ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን።”2 ጢሞቴዎስ 3:1

  •   “በዓለም ላይ ከስምንት ሰዎች አንዱ የአእምሮ ጤና እክል ያጋጥመዋል።” e

 የወጣቶች የአእምሮ ጤንነት ማሽቆልቆል” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

በ2024 ምን እንጠብቅ?

 መጪው 2024 ምን ነገሮችን ይዞ እንደሚመጣ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። ሆኖም በዓለም ላይ እየተከናወኑ ያሉት ነገሮች የአምላክ መንግሥት ወይም በሰማይ የተቋቋመው መስተዳድር በቅርቡ ሰብዓዊ መንግሥታትን በመተካት ለመከራና ለጭንቀት መንስኤ የሆኑትን ነገሮች በሙሉ እንደሚያስወግድ ይጠቁማሉ።—ዳንኤል 2:44፤ ራእይ 21:4

 እስከዚያው ግን ጭንቀት በሚሰማን ጊዜ አምላክ እንደሚረዳን መተማመን እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦

 “ፍርሃት በሚሰማኝ ጊዜ በአንተ እታመናለሁ።”መዝሙር 56:3

 በአምላክ እንደምንታመን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ወደፊት መከራ የሌለበት ጊዜ እንደሚመጣ ስለሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይበልጥ እንድትማር እንጋብዝሃለን። አንተም ሆንክ ቤተሰብህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎች ተጠቃሚ መሆን የምትችሉት እንዴት እንደሆነ ለማወቅ በነፃ የምንሰጠውን አሳታፊ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለምን አትሞክረውም?

a ጥቅምት 30, 2023 ፎሬን አፌርስ በተባለው ገጽ ላይ የወጣው “በጦርነት የታመሰ ዓለም፦ በዓለም ዙሪያ ከሚታየው የጦርነት መፋፋም በስተ ጀርባ ያለው ምክንያት ምንድን ነው?” የሚል ርዕስ፤ በኤማ ቢልስ እና በፒተር ሳሊስበሪ የተጻፈ።

b ኧርዝኩዌክ ኒውስ፣ ግንቦት, 2023 ላይ ያወጣው “2023፦ በዓለም ላይ እስካሁን ከተመዘገቡት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ሊባሉ የሚችሉ የምድር ነውጦች” የሚለው ርዕስ።

c የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ሐምሌ 27, 2023 “ዋና ጸሐፊው በአየር ንብረት ዙሪያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት የመክፈቻ ሐሳብ።”

d የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ “ዓለም አቀፍ የምግብ እጥረት።”

e የዓለም የጤና ድርጅት፣ “የ2023 የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን፣” ጥቅምት 10, 2023።