በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Anton Petrus/Moment via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

የዓለም ጦርነት አይቀሬ ይሆን?—⁠መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የዓለም ጦርነት አይቀሬ ይሆን?—⁠መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ብዙዎች፣ ባለፉት 30 ዓመታት በአገራት መካከል ያለው ሁኔታ እየተረጋጋ እንዲያውም እየተሻሻለ እንደሆነ ተሰምቷቸው ነበር። ይሁን እንጂ በቅርብ ጊዜ እየተከሰቱ ካሉት ነገሮች አንጻር ይህ አጠራጣሪ ሆኗል።

  •   “በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ በእስራኤልና በሄዝቦላ መካከል የተኩስ ልውውጥ መከፈቱ የጋዛ ጦርነት ወደ አጎራባች አገሮችም ይስፋፋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።”—ሮይተርስ፣ ጥር 6, 2024

  •   “ኢራን የምትደግፋቸው ቡድኖች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት እየሰነዘሩ ሲሆን የኑክሌር ፕሮግራሟም በድንገት አንሰራርቷል፤ በመሆኑም ሩሲያና ቻይና ከጎኗ የተሰለፉት ኢራን ለምዕራቡ ዓለም አዲስ ስጋት ፈጥራለች።”—ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ጥር 7, 2024

  •   “የሩሲያ ጥቃት በመላው ዩክሬን ውድመት እያስከተለ ነው።”—ዩ ኤን ኒውስ፣ ጥር 11, 2024

  •   “ቻይና በኢኮኖሚና በወታደራዊ ኃይል እየፈረጠመች መሄዷ፣ በታይዋን የብሔራዊ ኩራት ስሜት እየገነነ መምጣቱ እንዲሁም በቤጂንግ እና በዋሽንግተን መካከል ያለው ግንኙነት መሻከሩ በቀላሉ ጠብ እንዲጫር የሚያደርግ ሁኔታ ፈጥሯል።”—ዘ ጃፓን ታይምስ፣ ጥር 9, 2024

 መጽሐፍ ቅዱስ ዛሬ ስለምናየው ዓለም አቀፍ አለመረጋጋት የሚናገረው ነገር አለ? ሁኔታው ተባብሶ የዓለም ጦርነት ይፈነዳ ይሆን?

መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናችን ስላለው ሁኔታ ተንብዮአል

 መጽሐፍ ቅዱስ በአሁኑ ጊዜ ስለምናየው ስለየትኛውም ጦርነት ለይቶ አይናገርም። ሆኖም ጦርነት የምንኖርበት ዘመን መለያ እንደሚሆንና እዚህም እዚያም እየተቀሰቀሰ “ሰላምን ከምድር [እንደሚወስድ]” አስቀድሞ ተናግሯል።​—ራእይ 6:4

 የዳንኤል መጽሐፍ “በፍጻሜው ዘመን” ተፎካካሪ የሆኑ የዓለም ኃያላን እርስ በርስ ‘እንደሚገፋፉ’ ማለትም የበላይ ለመሆን እንደሚታገሉ አስቀድሞ ተናግሯል። በዚህ የሥልጣን ሽኩቻ ላይ ታላቅ ወታደራዊ ኃይል የሚያሳዩ ከመሆኑም ሌላ “ውድ ሀብቶች” ወይም ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ያፈስሳሉ።​—ዳንኤል 11:40, 42, 43

ጦርነት አይቀሬ ነው

 መጽሐፍ ቅዱስ የዓለም ሁኔታ ከመጥራቱ በፊት መደፍረሱ እንደማይቀር ይጠቁማል። ኢየሱስ “ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ . . . ሆኖ የማያውቅ . . . ታላቅ መከራ ይከሰታል” ብሏል። (ማቴዎስ 24:21) ይህ “ታላቅ መከራ” የሚደመደመው “ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን” በሚካሄደው አርማጌዶን በተባለው ጦርነት ነው።​—ራእይ 16:14, 16

 ይሁንና አርማጌዶን የሰውን ዘር አያጠፋም፤ እንዲያውም ይታደገዋል። አምላክ፣ አውዳሚ ለሆኑ በርካታ ጦርነቶች ምክንያት የሆነውን ሰብዓዊ አስተዳደር በአርማጌዶን አማካኝነት ያስወግደዋል። አርማጌዶን ዘላቂ ሰላም የሚያመጣው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ የሚከተሉትን ርዕሶች አንብብ፦