በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Justin Paget/Stone via Getty Images

የብቸኝነት ወረርሽኝ—መፍትሔው ምን ይሆን?

የብቸኝነት ወረርሽኝ—መፍትሔው ምን ይሆን?
  •   “በዩናይትድ ስቴትስ ከሚኖሩ ለአካለ መጠን የደረሱ ሰዎች መካከል ግማሽ ገደማ የሚሆኑት ብቸኝነት እንደሚሰማቸው ተናግረዋል፤ በተለይ ይህ ችግር ይበልጥ የሚስተዋለው ወጣቶች ላይ ነው።”—የብቸኝነትና የመገለል ወረርሽኝ፦ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የጤና ባለሥልጣን ማኅበራዊ ትስስርና ማኅበረሰብ ለጤና በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ላይ የሰጡት ሐሳብ፣ 2023

  •   “[የዓለም የጤና ድርጅት] በማኅበራዊ ትስስር ዙሪያ የሚሠራ አዲስ ቡድን ማቋቋሙን አሳውቋል፤ ዓላማውም ብቸኝነት ጤንነትን አደጋ ላይ የሚጥል አሳሳቢ ችግር መሆኑን ተገንዝቦ መፍትሔ መፈለግ፣ ለማኅበራዊ ትስስር ትኩረት መስጠት እንዲሁም ማንኛውም ገቢ ባላቸው አገሮች ውስጥ የመፍትሔ እርምጃዎችን ማጠናከር ነው።”—የዓለም የጤና ድርጅት፣ ኅዳር 15, 2023

 መጽሐፍ ቅዱስ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመመሥረት የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል።

ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮች

 ከሰዎች እንድትነጠሉ የሚያደርጓችሁን እንቅስቃሴዎች ቀንሱ። ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች መካከል ማኅበራዊ ሚዲያን ከልክ በላይ መጠቀም ይገኝበታል። እንዲህ ባሉ እንቅስቃሴዎች ፋንታ ከሰዎች ጋር በአካል መገናኘትና እውነተኛ ጓደኞችን ማፍራት የምትችሉባቸውን አጋጣሚዎች ፈልጉ።

  •   የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር፦ “እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።”—ምሳሌ 17:17

 ሌሎችን መርዳት የምትችሉባቸውን አጋጣሚዎች ፈልጉ። ለሌሎች ደግነት ማሳየታችን ከእነሱ ጋር ያለን ዝምድና እንዲጠናከር ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ደስተኞች እንድንሆንም ይረዳናል።

  •   የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር፦ “ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል።”—የሐዋርያት ሥራ 20:35

 ከሌሎች ጋር ጥሩ ጓደኝነት መመሥረት የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጣቸውን ተጨማሪ ምክሮች ለማግኘት ድረ ገጻችንን ተመልከት