በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ብቸኝነትን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

ብቸኝነትን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

 ብቸኝነት እየተሰማህ ነው? ከሆነ “በጣሪያ ላይ እንዳለች ብቸኛ ወፍ ሆንኩ” እንዳለው መዝሙራዊ ተሰምቶህ ይሆናል። (መዝሙር 102:7) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር ብቸኝነትን ለመቋቋም ይረዳሃል።

 መንፈሳዊነትህን አሳድግ

 ብቻህን ብትሆንም እንኳ መንፈሳዊ ፍላጎትህን ለማርካት ጥረት የምታደርግ ከሆነ ደስተኛ መሆን ትችላለህ። (ማቴዎስ 5:3, 6) ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በነፃ የሚገኙ መሣሪያዎች ይህን ለማድረግ ይረዱሃል።

የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አንብብ

  የሚከተሉት ጥቅሶች ለብዙ ሰዎች የመጽናኛ ምንጭ ሆነዋል። በአንዴ ብዙ ምዕራፎችን ከማንበብ ይልቅ ብቻህን የምታሳልፈውን ጊዜ በእያንዳንዱ ጥቅስ ላይ ለማሰላሰልና ለመጸለይ ልትጠቀምበት ትችላለህ።—ማርቆስ 1:35

በዓለም ላይ መጥፎ ነገሮች የሚደርሱበትን ምክንያት እወቅ

ከልክ በላይ አትጨነቅ

  በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የወጡትን ጽሑፎች ማንበብህ ብቻህን መሆንህ የሚያስከትልብህን ውጥረት ለመቋቋምና ‘መጨነቅህን ለመተው’ ይረዳሃል።—ማቴዎስ 6:25

ከጓደኞችህ ጋር አዘውትረህ ተነጋገር

  ጓደኝነት ለአእምሯዊም ሆነ ለስሜታዊ ጤንነትህ ጠቃሚ ነው፤ በተለይ በአካል ሰዎችን ማግኘት በማይቻልበት ጊዜ ጓደኝነት ይበልጥ አስፈላጊ ነው። ከቤት መውጣት የማትችል ከሆነ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ወይም በስልክ አማካኝነት ከጓደኞችህ ጋር ያለህን ዝምድና ማጠናከርና አዳዲስ ጓደኞች ማፍራት ትችላለህ። የሚከተሉት ርዕሶች “እውነተኛ ወዳጅ” ለማግኘት እንዲሁም ጥሩ ጓደኛ ለመሆን ይረዱሃል።—ምሳሌ 17:17

አካላዊ እንቅስቃሴ አድርግ

  መጽሐፍ ቅዱስ ‘የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚጠቅም’ ይናገራል። (1 ጢሞቴዎስ 4:8) በተለይ ብቻህን በምትሆንበት ጊዜ የአእምሮ ጤንነትህን ለመጠበቅና ደስተኛ ለመሆን ይረዳሃል። ከቤት መውጣት በማትችልበት ጊዜም ጭምር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የምትችልበት መንገድ ይኖራል።