በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Mary_Ukraine/stock.adobe.com

ነቅታችሁ ጠብቁ!

በፖለቲከኞች ላይ እምነት ማጣት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በፖለቲከኞች ላይ እምነት ማጣት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በ2024 ከዚህ ቀደም ታይቶ በማያውቅ መጠን በዓለም ዙሪያ በብዙ አገሮች ምርጫ ይካሄዳል። ሆኖም ብዙ ሰዎች በፖለቲከኞች ላይ ያላቸው እምነት ተሸርሽሯል።

  •   አንድ ጥናት እንዳሳየው በርካታ አሜሪካውያን፣ “ብዙዎቹ ፖለቲከኞች የሚያሳስባቸው የራሳቸውን ጥቅም ማሟላት” እንጂ ሕዝብን ማገልገል እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። a—ፒው የምርምር ማዕከል፣ መስከረም 19, 2023

 በተመሳሳይም ብዙ ወጣቶች ፖለቲከኞችን አያምኗቸውም።

  •   “በአሥራዎቹ ዕድሜ ያሉ ወጣቶች አንገብጋቢ የሆኑ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ ይሻሉ፤ ይሁንና ለችግሮቹ ፖለቲከኞች እልባት እንደማይሰጡ ይሰማቸዋል።”—ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ጥር 29, 2024

  •   “የሕዝብ አስተያየት እንደሚያሳየው ወጣቶች ከፖለቲከኞች ይልቅ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቪዲዮ የሚለቁ ሰዎችን ያምናሉ።”—ዘ ኮሪያ ታይምስ፣ ጥር 22, 2024

 ፖለቲከኞች ወደፊት የተሻለ ነገር እንደሚያመጡ እምነት ልንጥልባቸው እንችላለን? በዚህ ረገድ ማንን ማመን ይቻላል?

ሁሉን አትመን

 ሰዎች ‘ማን ላይ እምነት ልጣል?’ ብለው በጥሞና ማሰባቸው ተገቢ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “ተላላ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን አንድ በአንድ ያጤናል” ይላል።​—ምሳሌ 14:15

  •   የምታገኘው መረጃ እውነት መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንደምትችል ጠቃሚ ሐሳብ ለማግኘት “ከተሳሳተ መረጃ ራስህን ጠብቅ” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

 ልብ ልንለው የሚገባው ሌላው ነገር ደግሞ በጣም ሐቀኛና ቀና አስተሳሰብ ያላቸው ፖለቲከኞችም እንኳ ማድረግ የሚችሉት ነገር ውስን መሆኑን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚከተለውን ማሳሰቢያ የሚሰጠው ለዚህ ነው፦

  •   “ሰው ሊያድናችሁ ስለማይችል በሰብአውያን መሪዎች አትታመኑ።”​—መዝሙር 146:3 የ1980 ትርጉም

እምነት ልትጥልበት የምትችል መሪ

 አምላክ፣ የላቀ ችሎታ ያለውና እምነት የሚጣልበት መሪ እንደሾመ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፦ እሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (ሉቃስ 1:32, 33) ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ነው፤ የአምላክ መንግሥት የሚገዛው ከሰማይ ነው።​—ማቴዎስ 6:10

a ፒው የምርምር ማዕከል፣ “አሜሪካውያን በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ያላቸው ቅሬታ” መስከረም 2023