ነቅታችሁ ጠብቁ!
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ደስተኛ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ሕይወት አስተማማኝ አይደለም፤ ስለዚህ የሚያጋጥመንን ነገር ሁሉ መቆጣጠር አንችልም። ሆኖም ደስተኛ መሆናችን ብዙውን ጊዜ የተመካው ባለንበት ሁኔታ ላይ ሳይሆን በአመለካከታችን ላይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ደስተኛ ሰዎች ብዙ ችግር ቢያጋጥማቸውም እንኳ ‘ዘወትር በኑሯቸው እንደሚረኩ’ ይናገራል። (ምሳሌ 15:15 የ1980 ትርጉም) ታዲያ ይበልጥ ደስተኛ ለመሆን ምን ማድረግ እንችላለን? የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር የሚረዳን እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት።
ጭንቀትን መቋቋም
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።”—ምሳሌ 12:25
መጽሐፍ ቅዱስ ከመጠን በላይ እንዳንጨነቅ ይረዳናል። ይህን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጭንቀት ምን ይላል?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።
የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፍ
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።”—ምሳሌ 17:17
መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ጋር ጥሩ ወዳጅነት ለመመሥረት የሚረዳ ምክር ይሰጠናል፤ ይህም የብቸኝነት ስሜትን እንድናሸንፍ ይረዳናል። “ብቸኝነትን በወዳጅነት ማከም—መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ሊረዳህ ይችላል?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።
ለአምላክና ለሰዎች ፍቅር ማዳበር
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ። . . . ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።” a—ማቴዎስ 22:37-39
ጸሎት ለአምላክ ያለንን ፍቅር ለማሳደግ ይረዳናል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “አምላክ ጸሎታችንን ይሰማል?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።
“ወርቃማው ሕግ” ተብሎ የሚጠራውን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ለሌሎች ፍቅር ማሳየት እንችላለን። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ወርቃማው ሕግ ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።
መጽሐፍ ቅዱስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ደስተኛ ለመሆን የሚረዳህ እንዴት እንደሆነ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? በነፃ የምንሰጠውን አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን ለምን አትሞክረውም?
a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18