የይሖዋ ወዳጅ ሁን

ለልጆች ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚያስተምሩ አኒሜሽን ቪዲዮዎችን ተመልከት ወይም አውርድ።

ትልቁ የፍቅር መግለጫ

የኢየሱስ መሥዋዕት ከሁሉ የበለጠ ስጦታ የሆነው እንዴት ነው?

የሚያሳድገው አምላክ ነው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት ያስፈራሃል? ከሆነ ይሖዋ ይረዳሃል!

ይሖዋ አባታችን ነው

ይሖዋ ልክ እንደ አፍቃሪ አባት ያስብልሃል፤ ወደ እሱ ስትጸልይም ይሰማሃል።

ይሖዋ በጣም ይወድሃል

ዞዊ እንደ ኢየሱስ ይሖዋ እሷንም ሊወዳት እንደሚችል ተምራለች።

የይሖዋ ወዳጅ ሁን ቪዲዮ ማስተዋወቂያ፦ ይሖዋ በጣም ይወድሃል

ዞዊ ከሌሎች የተለዩ መሆን ጥሩ ነገር እንደሆነ ትማራለች።

ወደ ጥምቀት የሚያደርሱት እርምጃዎች

ሶፊያ ለመጠመቅ ብቃቱን ማሟላት የምትችለው እንዴት እንደሆነ ስትማር ተመልከት።

ያልተጠመቀ አስፋፊ ሁን

ካሌብ ያልተጠመቀ አስፋፊ ለመሆን ምን እንደሚያስፈልግ ተማረ።

ትምህርት 47፦ ምን ዓይነት ጓደኛ ልምረጥ?

ይሖዋ ጓደኞች እንዲኖሩህ ይፈልጋል፤ ሆኖም ጥሩ ጓደኛ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ትምህርት 45፦ አምላክን ባናየውም የምንታዘዘው ለምንድን ነው?

አምላክን ባናየውም የምንታዘዘው ለምንድን ነው? ሶፊያ ይህን ጥያቄ እንዴት እንደምትመልስ እንመልከት።

ትምህርት 44፦ ተስፋ አትቁረጡ

ሰዎች ምሥራቹን አንሰማም ሲሉ ምን ይሰማችኋል? ካሌብና ሶፊያ ምን እንዳደረጉ ተመልከቱ።

ትምህርት 43፦ ይሖዋ ጸሎት ይሰማል?

ይሖዋ እንዲረዳህ ጸልይ፤ ይሰማሃል።

የይሖዋ ወዳጅ ሁን ቪዲዮ ማስተዋወቂያ፦ ይሖዋ ጸሎት ይሰማል?

ይሖዋ የሶፊያን ጸሎት የመለሰላት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የይሖዋ ወዳጅ ሁን ቪዲዮ ማስተዋወቂያ፦ ይሖዋ ይቅር ይላል

ካሌብ ያጋጠመውን ፈተና የተወጣው እንዴት እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ?

ትምህርት 38፦ ባልንጀራህን ውደድ

የደጉ ሳምራዊን ምሳሌ በመከተል ባልንጀራህን እንደምትወድ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ትምህርት 37፦ የራስን ጥቅም መሠዋት

ኢየሱስ ሁልጊዜ የራሱን ጥቅም በመሠዋት ሌሎችን ይረዳ ነበር። አንተስ የኢየሱስን ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው?

ትምህርት 36፦ ቅጣት የፍቅር መግለጫ ነው

ይሖዋ የሚወዳቸውን የሚቀጣው ለምንድን ነው?

ትምህርት 35፦ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም

ጊዜ የይሖዋ ስጦታ ነው። ስለዚህ በጥበብ ልትጠቀምበት ይገባል።

ትምህርት 34፦ ሌሎችን መርዳት

አደጋ ያጋጠማቸውን ሰዎች ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላለህ?

ትምህርት 33፦ ይሖዋን ደስ አሰኘው

በየቀኑ የምታደርገው ነገር የይሖዋን ልብ ደስ ሊያሰኘው ይችላል።

ትምህርት 32፦ አገልግሎትህን በጥሩ መንገድ አከናውን

አገልግሎት ለመውጣት ዝግጁ ነህ? ወደ አገልግሎት ከመውጣትህ በፊት ማድረግ ያሉብህ ሦስት ነገሮች አሉ።

ትምህርት 31፦ ለይሖዋ ቤት ፍቅር ይኑርህ

የስብሰባ አዳራሹን በማጽዳቱ ሥራ ትካፈላለህ?

ትምህርት 30 ሐዘንን መቋቋም

የምንወደውን ሰው በሞት ስናጣ የሚሰማንን ሐዘን ለመቋቋም ምን ይረዳናል?

ትምህርት 29፦ ትሑት ሁን

ካሌብ ትሑት መሆን ምን ማለት እንደሆነ ተምሯል።

ትምህርት 28፦ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችን በጽናት መቋቋም

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የዮሴፍ ምሳሌ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችን በጽናት ለመቋቋም የሚረዳን እንዴት ነው?

ትምህርት 27፦ በገነት ውስጥ ስትኖር ይታይህ

በአዲሱ ዓለም ውስጥ ስትኖር ይታይሃል?

ትምህርት 26፦ ቤዛው

የኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት በአሁኑ ጊዜ የሚረዳን እንዴት ነው?

ትምህርት 25፦ ጓደኛ ማፍራት

በጉባኤ ውስጥ ጓደኞችህ ሊሆኑ የሚችሉት እነማን ናቸው?

ትምህርት 24፦ ሁሉንም ነገር ውብ አድርጎ የሠራው ይሖዋ ነው

ይሖዋ በጣም አስደናቂ ነገሮችን ሠርቷል! እናንተ በጣም የምትወዱት የትኛውን ነው?

ትምህርት 23፦ የይሖዋ ስም

የአምላክ ስም ያለውን ትርጉም ታውቃለህ?

ትምህርት 22፦ አንድ ወንድና አንዲት ሴት

አምላክ ጋብቻን አስመልክቶ ያወጣው መመሪያ ምንድን ነው? ጠቃሚ የሆነውስ ለምንድን ነው?

ትምህርት 21፦ ትዕግሥተኛ ሁን

ካሌብ ትዕግሥተኛ እንዲሆን የረዳው ምን እንደሆነ ለማወቅ ይህንን ቪዲዮ ተመልከት።

ትምህርት 20፦ እውነቱን ተናገር

ምንጊዜም እውነቱን መናገር ያለብህ ለምንድን ነው?

ትምህርት 19፦ ለጋስ ሁን

የይሖዋ ሕዝቦች ለጋስ በመሆናቸው ምን ነገር ማከናወን ችለዋል?

ትምህርት 18፦ ለይሖዋ ቤት አክብሮት ይኑርህ

ይሖዋ ለሚመለክበት ቤት ተገቢውን አክብሮት ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ትምህርት 17፦ ልጆቻችሁን ከጥቃት ጠብቁ

ካሌብና ሶፊያ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚረዳቸውን ጠቃሚ ምክር አግኝተዋል።

ትምህርት 16፦ በውጭ አገር ቋንቋ መስበክ

አንተ የምትናገረውን ቋንቋ መናገር ለማይችል ሰው ምሥራቹን መስበክ የምትችለው እንዴት ነው?

ትምህርት 15፦ በስብሰባ ላይ በደንብ ማዳመጥ

በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ በደንብ በማዳመጥ ትምህርት መቅሰም የሚኖርብን ለምንድን ነው?

ትምህርት 14፦ መልስ ለመስጠት መዘጋጀት

መልስ ለመስጠት ዝግጅት ማድረግ የምንችልባቸው አራት መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ትምህርት 13፦ ይሖዋ ደፋር እንድትሆን ይረዳሃል

ለሰዎች ስለ ይሖዋ በድፍረት እንድትናገር ምን ሊረዳህ ይችላል?

ትምህርት 12፦ ካሌብና ሶፊያ ቤቴልን ጎበኙ

ካሌብና ሶፊያ ቤቴልን ሲጎበኙ የተነሷቸውን ፎቶዎች ሲያዩ አብረህ እይ። ቤቴልን ስትጎበኝ እዚያ ምን አስደሳች ሥራ እንደሚሠራ ታውቃለህ።

የልጆችን ልብ የነካ ተከታታይ አኒሜሽን ቪዲዮ

የይሖዋ ምሥክሮች፣ ትናንሽ ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለመርዳት ተከታታይ አኒሜሽን ቪዲዮዎችን አዘጋጅተዋል። እነዚህ ቪዲዮዎች የሚዘጋጁት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

ትምህርት 11፦ በነፃ ይቅር በል

አንድ ሰው የሚያናድድ ነገር ቢያደርግብህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ትምህርት 10፦ ደግ ሁን፤ ያለህን አካፍል

ካሌብና ሶፊያ ያሏቸውን ነገሮች ሲካፈሉ የበለጠ ደስተኛ የሆኑት እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ይህን ቪዲዮ ተመልከት።

ትምህርት 9፦ ‘ሁሉንም ነገሮች የፈጠረው ይሖዋ ነው’

ይሖዋ የፈጠረው የመጀመሪያው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ከካሌብ ጋር አብረህ እየሄድህ ነገሮች የተፈጠሩበትን ቅደም ተከተል መማር ትችላለህ።

ትምህርት 8፦ ዕቃዎችህን በሥርዓት አስቀምጥ

ይሖዋ ለሁሉም ነገር ቦታ አዘጋጅቷል። አንተም ዕቃዎችህን በሥርዓት ማስቀመጥና ንጹሕ መሆን የምትችልበትን መንገድ መማር ትችላለህ!

ትምህርት 7፦ መስጠት ያስደስትሃል

ለሌሎች መስጠት የምትችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ምሳሌ መጥቀስ ትችላለህ?

ትምህርት 6፦ እባክህ እና አመሰግናለሁ

ካሌብ እነዚህን ቃላት መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ተማረ።

ትምህርት 5፦ አገልግሎት እንውጣ

ሶፊያ አገልግሎት ለመውጣት ዝግጁ ናት? ቪዲዮውን ተመልከት፤እንዲሁም አብረሃት የአገልግሎት ዝግጅት አድርግ።

ትምህርት 4፦ መስረቅ መጥፎ ነው

አምላክ ለስርቆት ያለው አመለካከት ምንድን ነው? ዘፀአት 20:15ን አንብብ። ቪዲዮውን በመመልከት ከካሌብ ጋር ተማር።

ትምህርት 3 ሁልጊዜ ጸልይ

ይህን ቪዲዮ አውርዳችሁ ለልጆቻችሁ በማሳየት ወደ ይሖዋ መጸለይ ያለባቸው መቼና የት እንደሆነ አስተምሯቸው።

ትምህርት 2፦ ይሖዋን ታዘዝ

በአንዳንድ መጫወቻዎች መጫወት የሌለብህ ለምንድን ነው? ይህን ቪዲዮ በመመልከት ካሌብ የይሖዋ ወዳጅ መሆን የቻለው እንዴት እንደሆነ ተማር።

ትምህርት 1፦ ወላጆችህን ታዘዝ

ወላጆችህን መታዘዝ ያለብህ ለምንድን ነው? ይህን ቪዲዮ በመመልከት የጥያቄውን መልስ ከካሌብ ጋር ሆነህ ተማር።

ይቅርታ ከመረጥከው ጋር የሚዛመድ ቃል የለም።