በአገልግሎት የምንጠቀምባቸው መግቢያዎች

ከሰዎች ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ውይይት ለመጀመር እንዲረዱህ ተብለው የተዘጋጁ ቪዲዮዎች።

ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው? ማስተዋወቂያ

ሕልውና ያገኘነው እንዴት እንደሆነ ማወቃችን የሕይወት ዓላማ ምን እንደሆነ ለማወቅ ሊረዳን ይችላል።

ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል!

በትዳርና በቤተሰብ ተቋም ላይ ጥቃት እየተሰነዘረ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደስተኛ ቤተሰብ እንዲኖረን የሚረዳ ምክር ይዟል።

ምሥራች መስማት ትፈልጋለህ?

በኢሳይያስ 52:7 ላይ በተገለጸው መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ የተሻለ ነገር እንደሚመጣ የሚያበስር ምሥራች ይዟል። ይህ ምሥራች ደስተኛ ቤተሰብ፣ እውነተኛ ጓደኞች እና ውስጣዊ ሰላም እንዲኖርህ ይረዳሃል።

የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሞቱብንን ሰዎች እዚሁ ምድር ላይ ዳግመኛ እንደምናገኛቸው ተስፋ ይሰጣል።

ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማወቅ ትፈልጋለህ?

ብዙ ሰዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማንነት ማወቅ ይፈልጋሉ። ስለ ማንነታችን ከእኛ ከራሳችን እንድትሰማ እንጋብዝሃለን።