የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል?
እያንዳንዱ ወጣት ‘ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል?’ የሚለውን አስፈላጊ ጥያቄ ሊያስብበት ይገባል። በሁለት የሚወዳቸው ነገሮች መካከል አጣብቂኝ ውስጥ የገባው አንድሬ የተባለው ወጣት ከራሱ ጋር የሚያደርገውን ትግል ስትመለከት ያወጣሃቸውን ግቦች መለስ ብለህ ገምግም። አንድሬ ምን ምርጫ ያደርግ ይሆን? የበለጠ የሚጠቅመው ምርጫስ የትኛው ነው? በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ወጣቶች የተደረገላቸው ቃለ ምልልስ በተጨማሪ ክፍሉ ውስጥ ተካትቷል፤ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ጠቃሚ ሐሳቦችን ታገኛለህ።