መግቢያ እና የምዕራፎቹ ይዘት

መግቢያ እና የምዕራፎቹ ይዘት

ቦታው የገሊላ ባሕር ዳርቻ ላይ ነው፤ ኢየሱስ ቅፍርናሆም በተባለችው ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ተራራ ላይ ሆኖ ለሕዝቡ ንግግር ሰጠ። በጣም ታዋቂ ከሆኑት የኢየሱስ ስብከቶች አንዱ የሆነው ይህ ንግግር በተለምዶ የተራራው ስብከት ተብሎ ይጠራል፤ ይህን ስብከት ማቴዎስ በተባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ከምዕራፍ 5 እስከ 7 ላይ ተመዝግቦ እናገኘዋለን። አንባቢው ከኢየሱስ ጥበብ ይማር ዘንድ ይህ ስብከት በዚህ ጽሑፍ ላይ ቀርቧል።

  • ምዕራፍ 5

    • ኢየሱስ በተራራ ላይ ማስተማር ጀመረ (1, 2)

    • ለደስታ ምክንያት የሚሆኑ ዘጠኝ ነገሮች (3-12)

    • ጨውና ብርሃን (13-16)

    • ኢየሱስ ሕጉን ሊፈጽም መጣ (17-20)

    • ቁጣን (21-26)፣ ምንዝርን (27-30)፣ ፍቺን (31, 32)፣ ቃለ መሐላን (33-37)፣ አጸፋ መመለስን (38-42)፣ ጠላትን መውደድን (43-48) በተመለከተ የተሰጠ ምክር

  • ምዕራፍ 6

    • “ግብዞች አትሁኑ” (1-4)

    • ጸሎትን በተመለከተ የተሰጠ ትምህርት (5-15)

      • የጸሎት ናሙና (9-13)

    • ጾም (16-18)

    • በምድር ሳይሆን በሰማይ ሀብት ማከማቸት (19-24)

    • አትጨነቁ (25-34)

      • የአምላክን መንግሥት ፈልጉ (33)

  • ምዕራፍ 7

    • “በሌሎች ላይ አትፍረዱ” (1-6)

    • ደጋግማችሁ ለምኑ፣ ፈልጉ፣ አንኳኩ (7-11)

    • ወርቃማው ሕግ (12)

    • ጠባቡ በር (13, 14)

    • “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” (15-23)

    • በዓለት ላይና በአሸዋ ላይ የተሠራ ቤት (24-27)

    • ሕዝቡ በኢየሱስ ትምህርት ተደነቁ (28, 29)