ኦሪጅናል መዝሙሮች

ዛሬ ነው ቀኔ

አማርኛ
ዛሬ ነው ቀኔ
https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/502900115/univ/art/502900115_univ_sqr_xl.jpg

ዛሬ ነው ቀኔ

ዛሬ ነው ቀኔ

አውርድ፦

  1. 1. ሕይወት አላፊ ነው በቅጽበት፤

    አለሁ ብሎ ማሰብ ዘበት።

    ጊዜውን ሳይሰጥ ፍቅሩን ለሚሹ፣

    ቆይ ነገ ሲል ያልፋል አይ ሰው፣ ፈራሹ!

    (አዝማች)

    ወዲያ ወዲህ ስል፣ ስባክን ሞልቶ ለማይሞላ፤

    ቅርቤ ያሉትን አልልም ችላ።

    ከሄደ ሄደ ነው ጊዜ፣ አይሸመት ከሌላ፤

    ይሄ ቀን አልፎ ለምን ልቆጭ ኋላ?

    ማን ያውቃል ነገን መክረሜ? አሁን ነው፣ ዛሬ ነው ቀኔ!

  2. 2. ውለታው ይገዝፋል ባሳቤ፤

    ሥራውን ሲያሰላስል ልቤ።

    አልሳሳም ብሠዋለት ጊዜዬን፤

    ቀን ከሌት ለሱ ብውል ባድር፣ ደስታዬ።

    (አዝማች)

    ወዲያ ወዲህ ስል፣ ስባክን ሞልቶ ለማይሞላ፤

    ፍቅሬን ለመግለጽ አልልም ችላ።

    ከሄደ ሄደ ነው ጊዜ፣ አይሸመት ከሌላ፤

    ይሄ ቀን አልፎ ለምን ልቆጭ ኋላ?

    ማን ያውቃል ነገን መክረሜ? አሁን ነው፣ ዛሬ ነው ቀኔ!

    (መሸጋገሪያ)

    ይሖዋ እስኪያድሰው ዘመኔን፣

    እርግማኑን አርቆ፤

    በቅርቡ ዕድሜ ከበረከት ጋር

    እስኪሰጠኝ መርቆ፤

    (አዝማች)

    ወዲያ ወዲህ ስል፣ ስባክን ሞልቶ ለማይሞላ፤

    ቅርቤ ያሉትን አልልም ችላ።

    ከሄደ ሄደ ነው ጊዜ፣ አይሸመት ከሌላ፤

    ይሄ ቀን አልፎ ለምን ልቆጭ ኋላ?

    ማን ያውቃል ነገን መክረሜ? አሁን ነው፣ ዛሬ ነው ቀኔ!