ለይሖዋ ዘምሩ—አዲስ መዝሙሮች
ይሖዋን ለማወደስና ለማምለክ የምንጠቀምባቸውን አዳዲስ መዝሙሮች አዳምጥ። ሙዚቃውንና ግጥሞቹን ካወረድክ በኋላ እነዚህን ግሩም መዝሙሮች ተለማመዳቸው።
መዝሙር 136
በሰማይ የተቋቋመው መንግሥት ይምጣልን!
ይህ ግሩም መዝሙር፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚመራውን የአምላክ መንግሥት በማቋቋሙ ይሖዋ አምላክን ለማመስገን የተዘጋጀ የውዳሴ መዝሙር ነው።
መዝሙር 141
ሰላም ወዳዶችን መፈለግ
ለሰዎች ፍቅር እንዳለን ብሎም የአምላክን ውድ በጎች ለማግኘት ትጋት የተሞላበት ፍለጋ እንደምናደርግ የሚገልጽ አስደሳች መዝሙር።
መዝሙር 142
ለሁሉም ዓይነት ሰዎች መስበክ
ስለ ይሖዋ ጥሩነት ዘምር፤ እንዲሁም ሁሉም ዓይነት ሰዎች የእሱ ወዳጆች እንዲሆኑ የመርዳት መብት በማግኘትህ የሚሰማህን አድናቆት በመዝሙር ግለጽ።
መዝሙር 149
ለቤዛው አመስጋኝ መሆን
ኢየሱስ በፈቃደኝነት ለእኛ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ መስጠቱ እስከ ዛሬ ከታዩት የፍቅር መግለጫዎች ሁሉ እጅግ የላቀ ነው እንድንል ያደርገናል፤ ይህ ስጦታ ይሖዋን ለዘላለም እንድናመሰግን ይገፋፋናል።
መዝሙር 151
የአምላክ ልጆች መገለጥ
ይሖዋ፣ የክርስቶስ ወንድሞችን ወደ ሰማይ የሚወስድበትንና ከክርስቶስ ጋር ድል የሚያደርጉበትን እንዲሁም አብረውት የሚነግሱበትን ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።