መዝሙር 113
ከአምላክ ያገኘነው ሰላም
-
1. ይሖዋን አወድሱ፤
ሰላም ይወዳል።
ጦርነትን ያስቀራል፤
ፍቅርን ያሰፍናል።
የሰላም አለቃ ነው፤
ልጁ ’የሱስም
ፍትሕ በማስፈን ባለም፣
ያመጣል ሰላም።
-
2. ጠበኝነትንና
ቁጣን ትተናል።
የጦር መሣሪያችንም
የሰላም ሆኗል።
ይህ ሰላም እንዳይጠፋ
ይቅር ባይ ’ንሁን፤
የክርስቶስ በጎች ነን፤
ሰላም ይኑረን።
-
3. ይሖዋን ስለታዘዝን
ሰላም ሰጥቶናል፤
ሞገሱን እንዳገኘን
በዚህ ይታያል።
መንግሥቱ እስኪያመጣ
ሰላም ለምድር፣
ሰላማዊ ለመሆን
ከልብ እንጣር።
(በተጨማሪም መዝ. 46:9ን፣ ኢሳ. 2:4ን እና ያዕ. 3:17, 18ን ተመልከት።)

