በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዓለማችን በመከራ የተሞላ ነው፤ ታዲያ ይህን መከራ ያመጣው አምላክ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ያመጣው አምላክ ነው?

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  • አዎ

  • አይደለም

  • ምናልባት

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“‘እውነተኛው አምላክ ክፉ ነገር ያደርጋል፤ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በደል ይፈጽማል’ ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው!” (ኢዮብ 34:10) በዓለም ላይ የምናየውን ክፋትና መከራ ያመጣው አምላክ አይደለም።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • በሰው ልጆች ላይ እየደረሰ ላለው መከራ በዋነኝነት ተጠያቂ የሆነው “የዚህ ዓለም ገዢ” ሰይጣን ዲያብሎስ ነው።—ዮሐንስ 14:30

  • በተጨማሪም ሰዎች የተሳሳተ ውሳኔ በማድረጋቸው ምክንያት ለችግርና ለመከራ የሚዳረጉበት ጊዜ አለ። —ያዕቆብ 1:14, 15

መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ? የሰው ልጆች በጋራ ጥረት ካደረጉ ችግሮችን ማስወገድ እንደሚችሉ የሚያምኑ ሰዎች አሉ፤ ሌሎች ደግሞ በዓለም ላይ ያለው ሁኔታ እንደማይሻሻል ይሰማቸዋል። አንተስ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ መከራን ያስወግዳል። “ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”—ራእይ 21:3, 4

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • ዲያብሎስ ያመጣብንን መከራ በሙሉ አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት ያስወግድልናል።—1 ዮሐንስ 3:8

  • ጥሩ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም በሰላም ይኖራሉ።—መዝሙር 37:9-11, 29