በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ሕይወት ይህ ብቻ ነው?

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት በጣም አጭር እንደሆነ ይሰማሃል?

‘ሕይወት ሲባል መጫወት፣ መሥራት፣ ትዳር መመሥረት፣ ልጅ መውለድ እንዲሁም ማርጀት ብቻ ነው?’ ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ? (ኢዮብ 14:1, 2) መጽሐፍ ቅዱስ ጠቢብ የነበሩ ሰዎችም እንኳ ይህ ጉዳይ ያሳስባቸው እንደነበር ይናገራል።—መክብብ 2:11ን አንብብ።

ታዲያ ሕይወት ከዚህ ያለፈ ትርጉም አለው? በቅድሚያ ግን ሕይወት ራሱ እንዴት ጀመረ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት አለብን። ብዙዎች አንጎላችንና ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን የተሠሩበትን አስደናቂ መንገድ ከተመለከቱ በኋላ ከዚህ ሁሉ በስተ ጀርባ ጠቢብ የሆነ ፈጣሪ መኖር አለበት ወደሚለው መደምደሚያ ደርሰዋል። (መዝሙር 139:14ን አንብብ።) ይህ ከሆነ ደግሞ ፈጣሪ እኛን የፈጠረበት ዓላማ አለው ማለት ነው! ይህን ዓላማ ማወቃችን ሕይወታችን ትርጉም እንዲኖረው ያደርጋል።

የሰው ልጆች የተፈጠሩበት ዓላማ ምንድን ነው?

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ጥንዶች የባረካቸው ሲሆን አስደሳች ሥራም ሰጥቷቸው ነበር። በመሆኑም እነሱን የፈጠረበት ዓላማ ምድርን እንዲሞሉ፣ ገነት እንዲያደርጉና ለዘላለም እንዲኖሩ ነበር።ዘፍጥረት 1:28, 31ን አንብብ።

የሰው ልጆች በአምላክ አገዛዝ ላይ በማመፃቸው የአምላክ ዓላማ በወቅቱ ሊፈጸም አልቻለም። ሆኖም አምላክ ለሰው ልጆችም ሆነ ለምድር ያለውን ዓላማ አልቀየረም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማዳን እንዲሁም ለምድር ያለውን ዓላማ ዳር ለማድረስ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጫ ይሰጣል! ስለሆነም አምላክ መጀመሪያ አስቦት የነበረውን ዓይነት ሕይወት እንድታጣጥም ይፈልጋል። (መዝሙር 37:29ን አንብብ።) አንተም ይህ የአምላክ ዓላማ ሲፈጸም ተጠቃሚ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ መማር ትችላለህ።