በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ሁሉም ሃይማኖቶች አምላክን ያስከብራሉ?

በዓለም ላይ ስለሚፈጸሙ ነገሮች ዜና ስታዳምጥ አንዳንድ ጊዜ በሃይማኖት ስም ብዙ የክፋት ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ አስተውለህ ይሆናል። በእውነተኛው አምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሁሉም ሃይማኖቶች አይደሉም። (ማቴዎስ 7:15) በእርግጥም በሐሰት ሃይማኖት የተነሳ አብዛኛው የሰው ልጅ ተሳስቷል።—1 ዮሐንስ 5:19ን አንብብ።

ይሁን እንጂ አምላክ መልካምና እውነት የሆነውን ነገር ለሚወዱ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ትኩረት ይሰጣል። (ዮሐንስ 4:23) አምላክ እንደዚህ ላሉት ሰዎች ከቃሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን እንዲማሩ ግብዣ እያቀረበላቸው ነው።1 ጢሞቴዎስ 2:3-5ን አንብብ።

እውነተኛውን ሃይማኖት መለየት የምትችለው እንዴት ነው?

ይሖዋ አምላክ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ለመጡ ሰዎች እውነትን በማስተማርና እርስ በርስ እንዲዋደዱ በማሠልጠን አንድነት እንዲኖራቸው እያደረገ ነው። (ሚክያስ 4:2, 3) በመሆኑም እውነተኛውን ሃይማኖት የሚከተሉ ሰዎችን እርስ በርስ ባላቸው ፍቅር ለይተህ ልታውቃቸው ትችላለህ።ዮሐንስ 13:35ን አንብብ።

ይሖዋ አምላክ ሁሉም ዓይነት ሰዎች በእውነተኛው አምልኮ አማካኝነት አንድነት እንዲኖራቸው እያደረገ ነው።—መዝሙር 133:1

እውነተኛ የአምላክ ተከታዮች እምነታቸውና አኗኗራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያደርጋሉ። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) በተጨማሪም የአምላክን ስም ያከብራሉ። (ዘፀአት 6:3) እንዲሁም የሰው ልጅ ብቸኛ ተስፋ የአምላክ መንግሥት እንደሆነ ለሰዎች ይናገራሉ። (ዳንኤል 2:44) የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ለሰዎች መልካም በማድረግ ‘ብርሃናቸው በሰው ፊት እንዲበራ’ ያደርጋሉ። (ማቴዎስ 5:16) በመሆኑም እውነተኛ ክርስቲያኖች፣ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ለማካፈል ወደ ሰዎች ቤት በመሄድም ተለይተው ይታወቃሉ።ማቴዎስ 24:14ን፣ የሐዋርያት ሥራ 5:42⁠ን እና 20:20ን አንብብ።