በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል ነው?

የአምላክ ቃል ለየት ያለ መሆን አለበት ብለህ እንደምትጠብቅ የታወቀ ነው፤ ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ የተለየ መጽሐፍ ነው። በቢሊዮን የሚቆጠሩ የዚህ መጽሐፍ ቅጂዎች በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ታትመዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ፣ ሰዎች ተለውጠው የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ የማድረግ ኃይል አለው።—1 ተሰሎንቄ 2:13ን እና 2 ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ በትክክል የሚናገሩ ትንቢቶችን መያዙ ይህን መጽሐፍ አምላክ እንዳጻፈው እንድንገነዘብ ያደርገናል። ሰዎች በራሳቸው ይህን ማድረግ አይችሉም። የኢሳይያስን መጽሐፍ እንደ ምሳሌ እንመልከት። ኢየሱስ ከመወለዱ ከመቶ ከሚበልጡ ዓመታት በፊት የተገለበጠ የዚህ መጽሐፍ ቅጂ በሙት ባሕር አቅራቢያ ባለ አንድ ዋሻ ውስጥ ተገኝቷል። ይህ ቅጂ የባቢሎን ከተማ ባድማ እንደምትሆን ይናገራል። ይህ ሁኔታ የተፈጸመው ኢየሱስ በምድር ላይ ካገለገለ ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው።—ኢሳይያስ 13:19, 20ን እና 2 ጴጥሮስ 1:20, 21ን አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው 1,600 በሚያህሉ ዓመታት ውስጥ ነው። አርባ የሚያህሉ ጸሐፊዎች በአንድ ጭብጥ ዙሪያ የሚያጠነጥንና እርስ በርሱ የማይጋጭ ሐሳብ ጽፈዋል። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? እነዚህ ሰዎች የጻፉት አምላክ እየመራቸው ስለሆነ ነው።—2 ሳሙኤል 23:2ን አንብብ።

አምላክ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን በመላእክት፣ በራእይና በሕልም አማካኝነት ያነጋግራቸው ነበር። በአብዛኛው አምላክ የሚፈልገውን ሐሳብ በአእምሯቸው ውስጥ ያስቀምጥና ጸሐፊዎቹ የፈለጉትን ቃላትና ሐረግ በመጠቀም የእሱን ሐሳብ እንዲያስተላልፉ ያደርጋል።—ራእይ 1:1⁠ን እና 21:3-5ን አንብብ።