መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 2013 | አምላክ ያስፈልገናል?
ብዙ ሰዎች አምላክ እንደማያስፈልጋቸው ወይም ስለ እሱ ለማሰብ ጊዜ እንደሌላቸው ይናገራሉ። በእርግጥ አምላክን ማወቅ የሚያስገኝልን ጥቅም አለ?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ይህን ጥያቄ ማንሳት ያስፈለገው ለምንድን ነው?
በአምላክ እንደሚያምኑ የሚናገሩ በርካታ ሰዎች የሚያደርጉት ምርጫ በእሱ መኖር እንደማያምኑ ያሳያል፤ ምክንያቱ ምንድን ነው?
የሕይወት ታሪክ
ይሖዋን ማገልገል የዕድሜ ልክ ሥራዬ እንዲሆን መረጥኩ
ቢል ዋልደን የምህንድስና ትምህርቱን ሊጨርስ ጥቂት ወራት ሲቀረው ይህን ሙያ በመተው ሙሉ በሙሉ የተለየ ሥራ ለመጀመር መረጠ። ሙሉ ጊዜውን አምላክን ለማገልገል መምረጡ ሕይወቱን የቀየረው እንዴት እንደሆነ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።
ወደ አምላክ ቅረብ
“እነሆ፣ ሁሉንም ነገር አዲስ አደርጋለሁ”
ሥቃይ፣ መከራና ሞት የተረሱ ነገሮች በሚሆኑበት ዓለም ውስጥ ለመኖር ትናፍቃለህ? አምላክ የሰጠውን ተስፋ የሚፈጽመው እንዴት ነው?
‘ከኮረብቶቿ መዳብ ቆፍረህ ታወጣለህ’
የቅርብ ጊዜ የአርኪኦሎጂ ግኝቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን መዳብ ጥቅም ላይ ይውል የነበረው እንዴት እንደሆነ ይገልጻሉ።
ልጆቻችሁን አስተምሩ
ኢየሱስ ክርስቶስ—በአእምሯችን ልናስበው የሚገባው እንዴት ነው?
ኢየሱስን ሁልጊዜ ሕፃን ልጅ እንደሆነ ብቻ አድርገን ማሰብ ይኖርብናል? ወደ እሱ የመጡት “ጠቢባን” እነማን ናቸው? ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ ምን እያደረገ ነው?
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ክርስቶስ ተመልሶ የሚመጣበት ዓላማ ምንድን ነው? የሚመለሰው እንዴት ነው? ከመጣ በኋላስ ምን ያደርጋል?
በተጨማሪም . . .
የይሖዋ ምሥክሮች የሚለውን መጠሪያ የምንጠቀመው ለምንድን ነው?
ይህን ስም ያገኘነው ከየት እንደሆነ ለማወቅ ጥቂት ጊዜ ወስደህ ምርምር እንድታደርግ እንጋብዝሃለን።