በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልትተማመንበት የምትችል ሃይማኖት አለ?

ልትተማመንበት የምትችል ሃይማኖት አለ?

በአንድ ሃይማኖት ውስጥ ያልጠበቅኸውን ነገር በማየትህ ተስፋ ቆርጠህ ከሆነ በየትኛውም ሃይማኖት ላይ እምነት መጣል አዳጋች ሊሆንብህ ይችላል። ይሁን እንጂ ልትተማመንበት የምትችል ሃይማኖት እንዳለ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። ኢየሱስ በምድር ሳለ ታማኝ ተከታዮቹን የአምላክን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች እንዲከተሉ አስተምሯቸዋል። በዛሬው ጊዜም ክርስቲያናዊ መሥፈርቶችን በሕይወታቸው ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ከልባቸው የሚጥሩ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች አሉ። ታዲያ እነዚህን ሰዎች የት ልታገኛቸው ትችላለህ?

ቀደም ካሉት ርዕሶች በአንዱ ላይ የተጠቀሰችው ኤስቴል እንዲህ ትላለች፦ “ከጊዜ በኋላ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ተገናኘሁና መጽሐፍ ቅዱስን መማር ጀመርኩ። ‘እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል’ የሚለውን በዮሐንስ 8:32 ላይ ያለውን ሐሳብ እውነተኝነት ለመረዳት ብዙ ጊዜ አልፈጀብኝም።”

ከዚህ በፊት የተጠቀሰው ሬይም እንደሚከተለው ብሏል፦ “ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ሳጠና በሰው ዘር ላይ እየደረሰ ላለው መከራ ተጠያቂው አምላክ እንዳልሆነ ተማርኩ። አምላክ በአሁኑ ጊዜ ክፋት እንዲኖር የፈቀደበት በቂ ምክንያት እንዳለውና በቅርቡ ደግሞ ክፋትን እንደሚያጠፋ ቃል መግባቱን ስረዳ በጣም ደስ አለኝ።”

መጥፎ ሥነ ምግባር ያላቸው ሰዎች በሞሉበት በዚህ ዓለም ውስጥ ጥሩ የሆነውን ማድረግ ከባድ እንደሚሆን የታወቀ ነው። ያም ቢሆን ይህን ማድረግ ይቻላል። ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳትና በሥራ ላይ ለማዋል እንዲችሉ የሚረዳቸው ቢያገኙ ደስ ይላቸዋል። የይሖዋ ምሥክሮች በመላው ዓለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በነፃ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምሩት ለዚህ ነው። በየሳምንቱ በርካታ ሰዎች ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚያጠኑ ሲሆን ይህም ወደ ፈጣሪያቸው ለመቅረብ እና ደስተኛ ሕይወት ለመምራት እያስቻላቸው ነው። *

የይሖዋ ምሥክሮችን፣ በሃይማኖታቸው እንዲተማመኑ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ለምን አትጠይቃቸውም?

የይሖዋ ምሥክሮችን ስታገኝ፣ በሃይማኖታቸው እንዲተማመኑ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ለምን አትጠይቃቸውም? የሚያስተምሩትን ነገር እንዲሁም ያተረፉትን ስም መርምር። ይህን ካደረግህ በኋላ፣ ልትተማመንበት የምትችል ሃይማኖት መኖር አለመኖሩን መወሰን ትችላለህ።

^ አን.5 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ተመልከት።