በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሥነ ምግባር—ሃይማኖቶችን ልትተማመንባቸው ትችላለህ?

ሥነ ምግባር—ሃይማኖቶችን ልትተማመንባቸው ትችላለህ?

ሲልቪያ የተባለች በሕክምና መስክ የተሰማራች ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ኮሌጅ እያለሁ አብረውኝ የተማሩት ብዙዎቹ ልጆች ሃይማኖተኛ እንደሆኑ ይናገሩ ነበር። ሆኖም ፈተና ላይ ይኮርጁ እንዲሁም ሕጋዊ ያልሆኑ ዕፆችን ይወስዱ ነበር። ሃይማኖታቸው በሕይወታቸው ላይ ምንም ለውጥ አላመጣም።”

ላዮኔል የሚባል አንድ ሰው ደግሞ እንዲህ በማለት ይናገራል፦ “የሥራ ባልደረቦቼ ይዋሻሉ፤ እንዲሁም ሳይታመሙ አሞናል ብለው ከሥራ ይቀራሉ። እነዚህ ሰዎች ሃይማኖት ቢኖራቸውም ሃይማኖታቸው፣ ከጌጥነት ባለፈ ሌላ ምንም ጥቅም እንደማይሰጥ የቤት ዕቃ ነው።”

ሃይማኖቶች አብዛኞቹ ሰዎች ጥሩ ሥነ ምግባር እንዲኖራቸው ማድረግ አልቻሉም። በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች “ለአምላክ ያደሩ መስለው” ቢታዩም “ኃይሉን ግን ይክዳሉ።” (2 ጢሞቴዎስ 3:5) የሃይማኖት መሪዎቻቸው ጥሩ ምሳሌ አልሆኑም፤ መንጎቻቸው ጥሩ ሥነ ምግባር እንዲኖራቸው የሚረዳቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትም ቢሆን አልሰጧቸውም። ከዚህ አንጻር ብዙዎች ምንም ዓይነት አኗኗር ቢኖራቸው አምላክ ግድ እንደማይሰጠው ቢያምኑ የሚያስደንቅ አይደለም።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ስሜት እንዳለውና ምግባራችን በእጅጉ እንደሚያሳስበው ይገልጻል። የጥንቶቹ እስራኤላውያን በአምላክ ላይ ባመፁ ጊዜ ‘አዝኖ’ ነበር። (መዝሙር 78:40) በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው ከልቡ ንስሐ ገብቶ መጥፎ ምግባሩን ሲለውጥ “በሰማይ ታላቅ ደስታ” ይሆናል። (ሉቃስ 15:7) አንድ ሰው የሰማዩ አባታችንን ግሩም ባሕርያት ሲያውቅ ለእሱ ያለው ፍቅር እያደገ ይሄዳል፤ ይህም አምላክ የሚወደውን እንዲወድና የሚጠላውን እንዲጠላ ያነሳሳዋል።—አሞጽ 5:15

ስለ ይሖዋ ምሥክሮችስ ምን ማለት ይቻላል?

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሶልት ሌክ ሲቲ፣ ዩታ የሚታተመው ዴዘርት ኒውስ የተሰኘው ጋዜጣ የይሖዋ ምሥክሮች “ጠንካራ ትስስር ያላቸው ቤተሰቦች እንዲሁም ሌሎችን የሚረዱና ሐቀኛ የሆኑ ዜጎች እንዲኖሩ አስችለዋል” ብሏል። ጋዜጣው አክሎ እንዲህ ብሏል፦ “አባላቱ የላቁ የሥነ ምግባር መሥፈርቶችን ይከተላሉ። ማጨስ፣ ከልክ በላይ መጠጣት፣ ዕፆችን አላግባብ መጠቀም፣ ቁማር መጫወት፣ የፆታ ብልግና እንዲሁም ግብረ ሰዶም ከአምላክ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያበላሹ ድርጊቶች እንደሆኑ ያምናሉ።”

የሃይማኖት መሪዎች፣ የአምላክን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች እንዲከተሉ መንጎቻቸውን ረድተዋቸዋል?

የይሖዋ ምሥክሮች ስለ አምላክ ባሕርያት መማራቸው የረዳቸው እንዴት ነው? ቀደም ሲል የተጠቀሰችው ሲልቪያ “በሕክምና መስክ ማጭበርበር የተለመደ ነገር ነው” በማለት ትናገራለች። “አንድ ሰው በቀላሉ እንዲህ ዓይነቱን አካሄድ ሊከተል ይችላል። ይሁን እንጂ ይሖዋ * ስለ ጉዳዩ ምን እንደሚሰማው ማወቄ ትክክል የሆነውን ነገር እንዳደርግ ይረዳኛል። ይህን በማድረጌ ደስተኛ ከመሆኔም ሌላ ውስጣዊ ሰላም አለኝ።” ሲልቪያ ሃይማኖቷ በሚያስተምራት መሠረት መኖሯ የተሻለ ሕይወት ለመምራት እንዳስቻላት ታምናለች።

^ አን.9 የአምላክ የግል ስም ይሖዋ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጿል።