በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ፦ ልትተማመንበት የምትችል ሃይማኖት አለ?

ሃይማኖትህን መመርመር ለምን አስፈለገ?

ሃይማኖትህን መመርመር ለምን አስፈለገ?

ሕይወትህን አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ይዞሃል እንበል፤ በመሆኑም ቀዶ ሕክምና ማድረግ ያስፈልግሃል። ቀዶ ጥገና የሚያደርግልህ ሐኪም የምትተማመንበት እንዲሆን ትፈልጋለህ፤ ምክንያቱም በሕይወት መትረፍህ የተመካው በእሱ ችሎታ ላይ ነው። ታዲያ ሐኪሙ ከሙያው አንጻር ምን ዓይነት ስም እንዳለው ማጣራቱ አስተዋይነት አይሆንም?

በተመሳሳይም ሃይማኖትህን በጥንቃቄ መመርመርህ ብልኅነት ነው። ምክንያቱም መንፈሳዊነትህ እንዲሁም የዘላለም ሕይወት ማግኘትህ የተመካው በያዝከው ሃይማኖት ላይ ነው።

ኢየሱስ፣ ትክክለኛውን ሃይማኖት ለማወቅ የሚያስችለን መሥፈርት ሰጥቶናል። “እያንዳንዱ ዛፍ በፍሬው ይታወቃል” ብሏል። (ሉቃስ 6:44) ታዲያ ሃይማኖትህ ምን ዓይነት ፍሬ እያፈራ ነው? የሃይማኖቱ መሪዎች ለገንዘብ ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ? የሃይማኖቱ አባላት ከጦርነትና ከሥነ ምግባር አንጻር የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች ይከተላሉ? ደግሞስ እምነት ሊጣልበት የሚችል ሃይማኖት አለ? መልሱን ለማግኘት ቀጣዮቹን ርዕሶች እንድትመረምር እንጋብዝሃለን።

“እያንዳንዱ ዛፍ በፍሬው ይታወቃል።”—ሉቃስ 6:44