መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 2013 | ልትተማመንበት የምትችል ሃይማኖት አለ?
ብዙ ሰዎች በሃይማኖታቸው ውስጥ ያልጠበቁትን ነገር በማየታቸው በሃይማኖት መተማመን ከባድ ሆኖባቸዋል። እምነት ልትጥልበት የምትችለው ሃይማኖት የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ሞክር።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ገንዘብ—ሃይማኖቶችን ልትተማመንባቸው ትችላለህ?
በአካባቢህ ያሉት ሃይማኖቶች ሰዎች ገንዘብ እንዲሰጡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጫና ያሳድራሉ? ይህስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ጦርነት—ሃይማኖቶችን ልትተማመንባቸው ትችላለህ?
ኢየሱስ ለተከታዮቹ ባልንጀራቸውን እንዲወዱ አስተምሯል። በዛሬው ጊዜ ያሉ ሃይማኖቶች ይህን ትእዛዝ እየተከተሉ ነው?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ሥነ ምግባር—ሃይማኖቶችን ልትተማመንባቸው ትችላለህ?
ብዙ የሃይማኖት መሪዎች በሥነ ምግባር ረገድ ጥሩ ምሳሌ አይሆኑም። አምላክ ሥነ ምግባራችን ያሳስበዋል?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ልትተማመንበት የምትችል ሃይማኖት አለ?
በአንድ ሃይማኖት ውስጥ ያልጠበቅኸውን ነገር በማየትህ ተስፋ ቆርጠህ ከሆነ በየትኛውም ሃይማኖት ላይ እምነት መጣል አዳጋች ሊሆንብህ ይችላል። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ሊረዳህ የሚችለው እንዴት ነው?
ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
ሁለተኛ ትዳር እንዲሰምር ማድረግ
በመጀመሪያ ትዳር ወቅት ጨርሶ ያልነበሩ ተፈታታኝ ሁኔታዎች በሁለተኛ ትዳር ላይ ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ታዲያ ሁለተኛ ትዳር የመሠረቱ ባልና ሚስት ሊሳካላቸው የሚችለው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
“አሁን፣ ዓለምን መለወጥ እንዳለብኝ አይሰማኝም”
የለውጥ አራማጅ የነበረ አንድ ሰው፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ለሰው ዘር እውነተኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበትን መንገድ ለማወቅ ያስቻለው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት
አምላክ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰው መከራ ያሳስበዋል?
አንዳንድ ሰዎች በዓለም ላይ ያለውን መከራ ሲያዩ አምላክ መኖሩን ይጠራጠራሉ። አምላክ እኛ መከራ ሲደርስብን ምን እንደሚሰማው ማወቅ ትፈልጋለህ? የአምላክ ቃል ይህን በተመለከተ ምን እንደሚል እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ሰዎች እርጅናን ለማስቀረት የተለያዩ ዘዴዎችን ሲሞክሩ ቆይተዋል። ሆኖም ከሞት ማምለጥ የቻለ ማንም የለም። ለምን?
በተጨማሪም . . .
የይሖዋ ምሥክሮች የራሳቸው ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎች የሚያናግሩት ለምንድን ነው?
የራሳቸው ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎች ለማነጋገር የሚያነሳሳን ምክንያት ምንድን ነው?