በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ይቻላል?

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው። አፍቃሪ ከሆነ አባት የተላከ ደብዳቤ ነው ማለት ይቻላል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) አምላክ እሱን እንዴት ማስደሰት እንደምንችል፣ ክፋት እንዲኖር ለምን እንደፈቀደ እንዲሁም ወደፊት ለሰው ልጆች ምን እንደሚያደርግ በቃሉ ላይ ገልጿል። ይሁንና የሃይማኖት አስተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት አዛብተዋል፤ በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ጨርሶ መረዳት እንደማይቻል ይሰማቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 20:29, 30

ይሖዋ አምላክ ስለ እሱ እውነቱን እንድናውቅ ይፈልጋል። በመሆኑም ልንረዳው የምንችል መጽሐፍ ሰጥቶናል።1 ጢሞቴዎስ 2:3, 4ን አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የምትችለው እንዴት ነው?

ይሖዋ፣ መጽሐፍ ቅዱስን መስጠት ብቻ ሳይሆን ይህን መጽሐፍ መረዳት የምንችልበት ዝግጅትም አድርጎልናል። ቃሉን እንዲያስተምረን ኢየሱስን ወደ ምድር ልኮታል። (ሉቃስ 4:16-21) ኢየሱስ የተለያዩ ጥቅሶችን በመጥቀስ አድማጮቹ የቅዱሳን መጻሕፍትን ሐሳብ እንዲረዱ አስችሏቸዋል።ሉቃስ 24:27, 32, 45ን አንብብ።

ኢየሱስ፣ እሱ የጀመረው ሥራ እንዲቀጥል ለማድረግ የክርስቲያን ጉባኤን አቋቁሟል። (ማቴዎስ 28:19, 20) በዛሬው ጊዜም የኢየሱስ እውነተኛ ተከታዮች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ የሚያስተምረውን ትምህርት እንዲያውቁ ሰዎችን ይረዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የምትፈልግ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው።የሐዋርያት ሥራ 8:30, 31ን አንብብ።