በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 ከአምላክ ቃል ተማር

ለዘላለም መኖር ይቻላል?

ለዘላለም መኖር ይቻላል?

ይህ ርዕስ በአእምሮህ ሊመላለሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን በማንሳት መልሶቹን መጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ የት ቦታ ላይ ማግኘት እንደምትችል ይጠቁምሃል። የይሖዋ ምሥክሮች ለጥያቄዎቹ በተሰጡት መልሶች ላይ ከአንተ ጋር ለመወያየት ፈቃደኞች ናቸው።

1. ዕድሜያችን አጭር እንደሆነ የሚሰማን ለምንድን ነው?

አንዳንድ ዔሊዎች 150 ዓመት ይኖራሉ፤ አንዳንድ ዛፎች ደግሞ የ3,000 ዓመት ዕድሜ አላቸው። ከዚህ አንጻር ሲታይ የሰው ልጆች ዕድሜ በጣም አጭር ነው። ይሁንና የሰው ልጆች ሕይወት ከዔሊም ሆነ ከዛፍ የበለጠ ትርጉም አለው። ይሖዋ አምላክ የሰው ልጆችን የፈጠረው በሙዚቃ፣ በስፖርት፣ ጥሩ ምግብ በመመገብ፣ በመማር፣ የተለያዩ ቦታዎችን በመጎብኘት እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ በመሆን መደሰት እንዲችሉ አድርጎ ነው። በተጨማሪም አምላክ በልባችን ውስጥ ለዘላለም የመኖር ፍላጎት እንዲኖር አድርጓል።—መክብብ 3:11ን አንብብ።

2. በእርግጥ ለዘላለም መኖር እንችላለን?

ይሖዋ ዘላለማዊ ነው። እሱ ፈጽሞ ሊሞት አይችልም። የሕይወት ምንጭ ስለሆነ ሌሎች ለዘላለም እንዲኖሩ ማድረግ ይችላል። (መዝሙር 36:9፤ 1 ጢሞቴዎስ 1:17 አ.መ.ት) ከዚህም በተጨማሪ፣ እሱን ለሚታዘዙ ሰዎች የዘላለም ሕይወት ለመስጠት ቃል ገብቷል። ያረጁ ሰዎች እንደገና ወጣት እንዲሆኑ ያደርጋል።—ኢዮብ 33:24, 25ን፣ ኢሳይያስ 25:8ን እና 33:24ን አንብብ።

ኢየሱስ አስደናቂ ተአምራት ፈጽሟል፤ ይህም ወደፊት ፍጹም ጤንነት አግኝተን ለዘላለም እንደምንኖር አምላክ የሰጠው ተስፋ መፈጸሙ እንደማይቀር ያሳያል። ኢየሱስ የተለያየ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ፈውሷል፤ ሌላው ቀርቶ የሞቱ ሰዎችን አስነስቷል።—ሉቃስ 7:11-15, 18, 19, 22ን አንብብ።

 3. የዘላለም ሕይወት የምናገኘው መቼ ነው?

አምላክ ለዘላለም እንድንኖር የሚፈልገው ግፍና ዓመፅ በሞላበት ዓለም ውስጥ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ለዘላለም የምንኖረው ገነት በሆነች ምድር ላይ ነው። አምላክ ፍላጎታችን ተሟልቶልን የሚያስፈራን ነገር በሌለበት ዓለም ላይ እንድንኖር ይፈልጋል። (መዝሙር 37:9, 29፤ ኢሳይያስ 65:21, 22) ምድር ገነት ስትሆን በሞት ያንቀላፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይነሳሉ። ከሞት የተነሱት ሰዎች አምላክን ለመታዘዝና እሱን ለማምለክ ፈቃደኛ ከሆኑ፣ ለዘላለም መኖር ይችላሉ።—ሉቃስ 23:42, 43፤ ዮሐንስ 5:28, 29ን አንብብ።

4. የዘላለም ሕይወት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

አምላክን ለማወቅ ሲባል ማንኛውም ጥረት ቢደረግ አያስቆጭም

መጨረሻ የሌለው ሕይወት ሊሰጠን የሚችለው አምላክ ብቻ ነው። በመሆኑም ስለ አምላክ በመማር ወደ እሱ መቅረብ ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስለ አምላክ እውቀት መቅሰምን ምግብ ከመብላት ጋር ያመሳስለዋል። (ማቴዎስ 4:4) ምግብ መመገብ አስደሳች ነው፤ ይሁንና ምግቡን ለመሥራት የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማግኘትም ሆነ ምግቡን ማዘጋጀት ጥረት ይጠይቃል። በተመሳሳይም መንፈሳዊ ምግብ መመገብ ጥረት ይጠይቃል። ይሁንና ወደ አምላክ ለመቅረብና የዘላለም ሕይወት ሽልማት ለማግኘት ሲባል እንዲህ ያለ ጥረት ቢደረግ የሚያስቆጭ ነው?—ሉቃስ 13:23, 24ን፣ ዮሐንስ 6:27ን እና ዮሐ 17:3ን አንብብ።