በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደስታ ስለሚገኝበት መንገድ

ደስታ ስለሚገኝበት መንገድ

 ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

ደስታ ስለሚገኝበት መንገድ

የደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?

ኢየሱስ በጣም ዝነኛ በሆነው የተራራ ስብከቱ መጀመሪያ ላይ ስለ ደስታ ተናግሮ ነበር። “በመንፈሳዊ ድሆች መሆናቸውን የሚያውቁ ደስተኞች ናቸው” ብሏል። (ማቴዎስ 5:3) ምን ማለቱ ነበር? በመንፈሳዊ የሚያስፈልገን ነገር ምንድን ነው?

በሕይወት ለመቀጠል እንደ እንስሳት ሁሉ እኛም መተንፈስ፣ መጠጣትና መብላት አለብን። ደስተኛ ለመሆን ግን እንስሳት የሌላቸው እኛ ሊሟላልን የሚገባ አንድ ነገር አለ፤ ይኸውም የሕይወትን ዓላማ የመረዳት ፍላጎት ነው። ይህን ፍላጎታችንን ማርካት የሚችለው የሕይወት ፈጣሪ ብቻ ነው። ስለሆነም ኢየሱስ “ሰው ከይሖዋ አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ ሊኖር አይችልም” በማለት ተናግሯል። (ማቴዎስ 4:4) በመንፈሳዊ ድሆች መሆናቸውን የሚያውቁ ደስተኞች ናቸው፤ ምክንያቱም ‘ደስተኛ ወደሆነው አምላክ’ ወደ ይሖዋ ይቀርባሉ፤ እሱም ለደስታ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነገር ይኸውም ተስፋን ይሰጣቸዋል።—1 ጢሞቴዎስ 1:11

ኢየሱስ ተስፋ የሰጠው እንዴት ነው?

ኢየሱስ “ገሮች ደስተኞች ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና” ብሏል። (ማቴዎስ 5:5) ኢየሱስ የታመሙ ሰዎችን በመፈወስና የሞቱ ሰዎችን በምድር ላይ ዳግመኛ ሕያው በማድረግ ለሰዎች ተስፋ ሰጥቷል። በተጨማሪም የመጣው የተስፋ መልእክት ይዞ ነው። “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ በልጁ እንደሚያምን በተግባር የሚያሳይ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል” ሲል ገልጿል። (ዮሐንስ 3:16) አምላክን የሚታዘዙ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ። ገር በሆኑና ፈጽሞ በማያረጁ ሰዎች መካከል ሆኖ መኖር ምን ሊመስል እንደሚችል እስቲ አስበው። የአምላክ ቃል “በተስፋው ደስ ይበላችሁ” ማለቱ ምንም አያስገርምም። (ሮም 12:12) ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ ደስታ ማግኘት የምንችልበትንም መንገድ ገልጿል።

 ኢየሱስ ያስተማረው ስለ የትኛው አስደሳች የሕይወት መንገድ ነው?

ኢየሱስ ከሰዎች ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት፣ ስለ ትዳር፣ ስለ ትሕትናና ቁሳዊ ነገሮችን በተመለከተ ተገቢውን አመለካከት ስለ መያዝ ጠቃሚ ምክር ሰጥቷል። (ማቴዎስ 5:21-32፤ 6:1-5, 19-34) የኢየሱስን ምክር መከተልህ ደስተኛ እንድትሆን ይረዳሃል።

ለጋስ መሆን ደስታ ያስገኛል። (የሐዋርያት ሥራ 20:35) ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ አካለ ስንኩላንን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውሮችን ጥራ፤ ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ ደስተኛ ትሆናለህ።” (ሉቃስ 14:13, 14) ደስተኛ መሆን የሚቻለው ሌሎች ሰዎች ደስተኛ እንዲሆኑ በመርዳት እንጂ ስለ ራስ ደስታ ብቻ በማሰብ አይደለም።

ከሁሉ የላቀው የደስታ ምንጭ ምንድን ነው?

ለሰዎች የተለያዩ ነገሮችን ማድረግ ደስታ ሊያስገኝ ይችላል፤ ለአምላክ ማድረግ ግን የበለጠ ደስታ ያስገኛል። በዚህ መንገድ የሚገኘው ደስታ ልጆቻቸውን የሚወዱ ወላጆች ከሚያገኙት ደስታ እንኳ የላቀ ነው። ኢየሱስ በሕዝብ ፊት እያስተማረ በነበረበት ወቅት የተፈጸመው ሁኔታ ይህን ግልጽ ያደርግልናል። “ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ‘አንተን የተሸከመ ማህፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ደስተኞች ናቸው!’ አለችው። እሱ ግን ‘ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!’ አለ።”—ሉቃስ 11:27, 28

ኢየሱስ ራሱ በሰማይ የሚገኘውን አባቱን ፈቃድ በማድረግ ደስታና እርካታ አግኝቷል። የአምላክ ፈቃድ ደግሞ ሰዎች ስለ ዘላለም ሕይወት ተስፋ እንዲሰሙ ነው። በአንድ ወቅት ኢየሱስ የሚናገረውን መልእክት የመስማት ፍላጎት ላደረባት አንዲት ሴት ይህን ተስፋ ከገለጸ በኋላ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውን መፈጸም ነው” በማለት ተናግሯል። (ዮሐንስ 4:13, 14, 34) አንተም አምላክን የሚያስደስተውን ነገር በማድረግ ይኸውም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሰዎች በመናገር የሚገኘውን ደስታ ማጣጣም ትችላለህ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተመልከት።

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

እውነተኛ ደስታ የሚገኘው የሕይወት ትርጉም ምን እንደሆነ ለማወቅ ያለንን ፍላጎት በማርካት ነው