በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

 ይህን ያውቁ ኖሯል?

ጉንዳኖች በእርግጥ በበጋ ወቅት ምግባቸውን ያከማቻሉ? በመከር ወቅትስ ቀለባቸውን ይሰበስባሉ?

ምሳሌ 6:6-8 እንዲህ ይላል፦ “አንተ ታካች፤ ወደ ጕንዳን ሂድ፤ ዘዴውን አስተውለህ ጠቢብ ሁን፤ አዛዥ የለውም፤ አለቃም ሆነ ገዥ የለውም፤ ሆኖም ግን በበጋ ምግቡን ያከማቻል፤ በመከርም ወቅት ቀለቡን ይሰበስባል።”

እርግጥ ነው፣ በርካታ የጉንዳን ዝርያዎች ምግባቸውን ይሰበስባሉ። ሰለሞን በዚህ ጥቅስ ላይ የገለጻቸው በእስራኤል በብዛት ይገኙ የነበሩትንና የመከር ጉንዳን (ሜሰር ሰሚረፈስ) ተብለው የሚጠሩትን የጉንዳን ዝርያዎች ሳይሆን አይቀርም።

አንድ ምንጭ እንደገለጸው “የመከር ጉንዳኖች ጥሩ የአየር ንብረት ባለበት ወቅት መኖሪያቸውን ትተው ምግብ ፍለጋ ይሄዳሉ፤ . . . [እንዲሁም] ሞቃታማ በሆኑት ወራት ፍሬዎችን ይሰበስባሉ።” ፍሬዎችን ከተክሎች አሊያም ከመሬት ሊለቅሙ ይችላሉ። እነዚህ ጉንዳኖች ቤታቸውን ከምድር በታች የሚሠሩት እህል በሚገኝባቸው በማሳዎች፣ በጎተራዎች ወይም በአውድማዎች አካባቢ ነው።

ጉንዳኖች በመኖሪያቸው ውስጥ ቀለባቸውን የሚያከማቹት እርስ በርስ ተያያዥነት ባላቸው በመደዳ በተሠሩ ክፍሎች ውስጥ ነው። የጎተራቸው ስፋት እስከ 12 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ሲሆን ቁመቱ ደግሞ አንድ ሴንቲ ሜትር ይሆናል። በሚገባ የተደራጁት የመከር ጉንዳኖች “ከመኖሪያቸው ውጪ ምግብ ወይም ውኃ ፍለጋ ሳይሄዱ ከ4 ወራት በላይ” መቆየት እንደሚችሉ ይነገራል።

የንጉሥ ጠጅ አሳላፊ መሆን ምን ነገሮችን ይጨምር ነበር?

ነህምያ የፋርስ ንጉሥ የነበረው የአርጤክስስ ጠጅ አሳላፊ ነበር። (ነህምያ 1:11) በጥንቱ ሩቅ ምሥራቅ ቤተ መንግሥት ውስጥ የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ሆኖ መሥራት ዝቅተኛ ሥራ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ ይህ ሥራ የሚሰጠው ሰው ከፍተኛ ሥልጣን ነበረው። ጠጅ አሳላፊዎችን የሚያሳዩ ጥንታዊ ሥነ ጽሑፎችና በርካታ ሥዕላዊ መግለጫዎች ነህምያ በፋርስ ቤተ መንግሥት የነበረውን ድርሻ በተመለከተ በርካታ ነገሮችን እንድናውቅ ይረዱናል።

ጠጅ አሳላፊው ንጉሡ የተመረዘ መጠጥ እንዳይጠጣ አስቀድሞ የንጉሡን ወይን ጠጅ ይቀምስ ነበር። በመሆኑም ጠጅ አሳላፊው በንጉሡ ዘንድ ትልቅ አመኔታ ነበረው። ኤድወን ያማውቺ የተባሉ ታሪክ ጸሐፊ እንዲህ ብለዋል፦ “በፋርስ ቤተ መንግሥት [በአከመኒድ ሥርወ መንግሥት] የተለመደ በነበረው ሽኩቻና ሴራ ምክንያት እምነት የሚጣልባቸው ባለሟሎች ማግኘት በጣም አስፈላጊ እንደነበር ያሳያል።” በተጨማሪም ጠጅ አሳላፊው በንጉሡ ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ተወዳጅ ባለሥልጣን ነበር። በየዕለቱ ከንጉሠ ነገሥቱ አጠገብ የሚሠራ መሆኑ ወደ ንጉሡ መግባት ያለበት ማን እንደሆነ የመወሰን መብት እንዲኖረው ሳያደርግ አልቀረም።

ጠጅ አሳላፊ እንዲህ ያለ ሥልጣን ያለው መሆኑ ነህምያ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ቅጥሩን መልሶ እንዲገነባ ንጉሡ ፈቃድ የሰጠበትን ምክንያት ግልጽ ያደርግልናል። ነህምያ በንጉሡ ዘንድ ትልቅ ቦታ ይሰጠው የነበረ ሰው ሳይሆን አይቀርም። ዚ አንከር ባይብል ዲክሽነሪ እንደገለጸው “ንጉሡ ‘መቼ ትመለሳለህ?’ ከማለት ሌላ ምንም ማለት አልቻለም።”—ነህምያ 2:1-6

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሥዕላዊ መግለጫ]

በፋርስ ከነበረው የፐርሰፐሊስ ቤተ መንግሥት የተገኘ ምስል

[ሥዕላዊ መግለጫ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ጠጅ አሳላፊ

ዘውድ የደፋው ልዑል ዜርሰስ

ታላቁ ዳርዮስ

[ምንጭ]

© The Bridgeman Art Library International