በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ማላዊ፣ አፍሪካ

አንባቢያን የሚያነሱት ጥያቄ . . .

የመንግሥት አዳራሽ ምንድን ነው?

የመንግሥት አዳራሽ ምንድን ነው?

የመንግሥት አዳራሽ የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴያቸውን የሚያከናውኑበት የአምልኮ ቦታ ነው። በዓለም ዙሪያ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት አዳራሾች አሉ። ከ105,000 በላይ የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች በየሳምንቱ በእነዚህ አዳራሾች ውስጥ ይሰበሰባሉ።

እያንዳንዱ የመንግሥት አዳራሽ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም የሚደረግበትና ንግግር የሚሰጥበት አዳራሽ አለው። እያንዳንዱ አዳራሽ ስብሰባዎቹን የሚመሩ ሰዎች የሚጠቀሙበት መድረክ አለው። በአብዛኛው አዳራሾቹ ከ100 እስከ 300 መቀመጫዎች አሏቸው። በተጨማሪም የመንግሥት አዳራሾቹ አንድ ወይም ከአንድ በላይ ተጨማሪ ክፍሎች፣ ቢሮ እንዲሁም አነስተኛ ቤተ መጻሕፍት አሏቸው፤ እነዚህ ቤተ መጻሕፍት ማንኛውም የጉባኤ አባል ምርምር ማድረግ እንዲችል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጽሑፎችና ሌሎች የማመሳከሪያ መጻሕፍት አሏቸው።

ይሁን እንጂ በእነዚህ የመንግሥት አዳራሾች ውስጥ በሌሎች የሕዝበ ክርስትና ቤተ ክርስቲያኖች እንደሚገኙት ያሉ ሃይማኖታዊ ሥዕሎችና ቅርጻ ቅርጾች አታገኝም። የሚታዩ መሠዊያዎች፣ ምሥሎች ወይም መስቀሎች የሉም። ለምን? የይሖዋ ምሥክሮች እነዚህን ነገሮች መጠቀም “ከጣዖት አምልኮ ሽሹ” ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ ጋር እንደሚቃረን ያምናሉ። (1 ቆሮንቶስ 10:14፤ ዮሐንስ 4:24) ብዙ አብያተ ክርስቲያናትና ቤተ መቅደሶች እጅግ ያጌጡና የተንቆጠቆጡ ናቸው። ከዚህ በተቃራኒ እነዚህ የመንግሥት አዳራሾች የሚገነቡት ያልተወሳሰበ ንድፍ ኖሯቸው ለሚፈለገው ዓላማ ጥቅም መስጠት በሚችሉበት መንገድ ነው። ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ለሕንፃው ሳይሆን በሕንፃው ውስጥ ለሚካሄደው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ነው።

ይህ መሰብሰቢያ ቦታ የመንግሥት አዳራሽ ተብሎ የሚጠራው ለምንድን ነው? በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ የሚካሄዱት ስብሰባዎች በዋነኝነት የሚያተኩሩት በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጥና የኢየሱስ አገልግሎት ዋና መልእክት በሆነው ‘በአምላክ መንግሥት’ ላይ ነው። (ሉቃስ 4:43) በመሆኑም ከ1930ዎቹ ዓመታት ወዲህ ለመሰብሰቢያ አዳራሾች መጠሪያ የሆነው ይህ ስም የሕንፃውን ዓላማ በሚገባ የሚወክል ነው፤ የመንግሥት አዳራሽ እውነተኛውን አምልኮ ለማስፋፋትና ‘የመንግሥቱን ምሥራች’ ለመስበክ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል። (ማቴዎስ 24:14) ስለሆነም በመንግሥት አዳራሾች ውስጥ ማንኛውም ማኅበራዊም ሆነ የንግድ እንቅስቃሴ አይካሄድም። ለአዳራሹ ግንባታም ሆነ ከአዳራሹ ጋር ለተያያዙ ሌሎች ወጪዎች በሙሉ የሚያስፈልገው ገንዘብ የሚገኘው በፈቃደኝነት በሚደረግ መዋጮ አማካኝነት ነው። ሙዳየ ምጽዋት በፍጹም አይዞርም። ከዚህ ይልቅ ማንኛውም ሰው መዋጮ ማድረግ እንዲችል የተወሰነ ቦታ ላይ የመዋጮ ሣጥን ይቀመጣል።

በዓለም ዙሪያ የሚገኙት የመንግሥት አዳራሾች ዓላማቸው ተመሳሳይ ቢሆንም የተለያየ መጠንና አሠራር አላቸው። የአዳራሾቹ አሠራር በአገሪቱ የአየር ንብረት፣ በዚያ በሚገኙት ቁሳቁሶችና በአካባቢው በሚኖሩት የይሖዋ ምሥክሮች የገንዘብ አቅም የተመካ ነው። አንዳንዶቹ አዳራሾች ከሸክላ፣ ከእንጨት ወይም ከድንጋይ ሊሠሩ ይችላሉ። ሌሎች አዳራሾች ደግሞ በአንድ ወይም በሁለት በኩል ግድግዳ ላይኖራቸው ይችላል፤ ግድግዳ ካላቸው ግድግዳው ከቀርከሃ ይሠራና ጣሪያው በሣር ይሸፈናል።

ማንም ሰው በየትኛውም የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ በሚደረገው ስብሰባ ላይ መገኘት ይችላል። (ዕብራውያን 10:25) እንዲያውም በየሳምንቱ ለጉባኤው አባላትም ሆነ ለአዲሶች የሚሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ የሕዝብ ንግግር ይሰጣል። ታዲያ በአካባቢህ ወደሚገኝ የመንግሥት አዳራሽ ሄደህ ለምን አትሰበሰብም?

እንግሊዝ፣ ታላቋ ብሪታንያ