በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የተሳሳተ ትምህርት 5፦ ማርያም የአምላክ እናት ናት

የተሳሳተ ትምህርት 5፦ ማርያም የአምላክ እናት ናት

ይህ የተሳሳተ ትምህርት የመነጨው ከየት ነው?

“ለአምላክ እናት አምልኮ አከል ክብር መስጠት ይበልጥ የተስፋፋው . . . አረማዊ አምልኮ ይከተሉ የነበሩ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን በጎረፉበት ወቅት ነው። . . . [ወደ ክርስትና የተለወጡት አረማውያን እንዲህ ያለውን] የአምልኮ ቅንዓትንና ሃይማኖተኛነትን ያዳበሩት ለሺህ ዓመታት ‘ታላቋ እናት’ እና ‘ድንግል አምላክ’ የተባለችውን ሴት አምላክ ያመልኩ በነበረበት ወቅት ነው።”—ዘ ኒው ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ (1988)፣ ጥራዝ 16፣ ገጽ 326 እና 327

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“እነሆ፤ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑል ልጅም ይባላል፤ . . . የሚወለደው ቅዱሱ ሕፃን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።”—ሉቃስ 1:31-35 አ.መ.ት

ይህ ጥቅስ ማርያም “የእግዚአብሔር ልጅ” እናት እንጂ የራሱ የእግዚአብሔር እናት እንዳልሆነች በግልጽ ያሳያል። ‘ሰማይ እንኳ ይይዘው ዘንድ የማይችለውን’ አምላክ ማርያም በማህፀኗ ልትይዝ ትችላለች? (1 ነገሥት 8:27) ማርያምም ቢሆን የእግዚአብሔር እናት እንደሆነች በጭራሽ ተናግራ አታውቅም። ማርያም የማን እናት ስለመሆኗ ግራ መጋባት እንዲፈጠር ያደረገው የሥላሴ ትምህርት ነው። በ431 ዓ.ም. የኤፌሶን ጉባኤ፣ ማርያም ቲኦቶኮስ (ይህ የግሪክ ቃል “ወላዲተ አምላክ” የሚል ትርጉም አለው) ወይም “የአምላክ እናት” እንደሆነች ሲገልጽ የማርያም አምልኮ እንዲጀመር መንገድ ከፈተ። ይህ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ የተካሄደበት የኤፌሶን ከተማ፣ ለበርካታ ዘመናት አርጤምስ የተባለችው የመራባት አምላክ የምትመለክበት የጣዖት አምልኮ ማዕከል ሆኖ ነበር።

በዚህም የተነሳ ‘ከሰማይ የወረደው’ የአርጤምስ ምስል አምልኮ በርካታ ገጽታዎች (ለምሳሌ የማርያምን ምስል ይዞ በአደባባይ መዞር) በማርያም አምልኮ ውስጥ እንዲካተቱ ተደረገ። (የሐዋርያት ሥራ 19:35) ወደ ክርስትና ትምህርቶች ቀስ በቀስ ሰርገው ከገቡት ልማዶች መካከል ሌላው ደግሞ የማርያምንና የሌሎችን ምስል ለአምልኮ መጠቀም ነው።

እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አወዳድር፦ ማቴዎስ 13:53-56፤ ማርቆስ 3:31-35፤ ሉቃስ 11:27, 28

እውነታው፦

ማርያም የአምላክ ልጅ እናት እንጂ የራሱ የአምላክ እናት አይደለችም። ስለ ሥላሴ የሚገልጸው የተሳሳተ ትምህርት ማርያም፣ ወላዲተ አምላክ ተብላ እንድትመለክ ምክንያት ሆኗል