በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የተሳሳተ ትምህርት 3፦ ጥሩ ሰዎች በሙሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ

የተሳሳተ ትምህርት 3፦ ጥሩ ሰዎች በሙሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ

ይህ የተሳሳተ ትምህርት የመነጨው ከየት ነው?

የኢየሱስ ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ፣ በሁለተኛው መቶ ዘመን መባቻ ላይ የጥንቶቹ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሰፊ ተቀባይነት ማግኘት ጀመሩ። እነዚህ ሰዎች የሚያስተምሩትን ትምህርት በተመለከተ ዘ ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ (2003)፣ ጥራዝ 6፣ ገጽ 687 እንዲህ ይላል፦ “ከሞት በኋላ ከሥጋ የተለየው ነፍስ አስፈላጊው የመንጻት ሥርዓት ከተደረገለት በኋላ ወዲያውኑ ወደ ሰማይ ይሄዳል የሚለው ትምህርት በስፋት ተቀባይነት አግኝቷል።”

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ገሮች ደስተኞች ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።”—ማቴዎስ 5:5

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በሰማይ ‘ቦታ እንደሚያዘጋጅላቸው’ ቃል ቢገባላቸውም ወደ ሰማይ የሚሄዱት ሁሉም ጻድቃን እንዳልሆኑ ጠቁሟል። (ዮሐንስ 3:13፤ 14:2, 3) ኢየሱስ የአምላክ ፈቃድ “በሰማይ እየሆነ እንዳለ ሁሉ በምድርም” እንዲሆን መጸለዩንም ማስታወስ ያስፈልጋል። (ማቴዎስ 6:9, 10) ለጻድቃን የተዘጋጀው ተስፋ፣ ከክርስቶስ ጋር በሰማይ መግዛት አሊያም በምድር ላይ ለዘላለም መኖር ነው፤ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በሰማይ ከክርስቶስ ጋር የሚገዙ ሲሆን አብዛኛው የሰው ዘር በምድር ላይ ይኖራል።—ራእይ 5:10

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ የምታከናውነውን ሥራ በተመለከተ ያላት አመለካከት ተቀየረ። ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ? ዘ ኒው ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደሚገልጸው ቤተ ክርስቲያን፣ ሰዎች የአምላክን መንግሥት መምጣት እንዲጠብቁ ከማበረታታት ይልቅ ተስፋቸውን በእሷ ላይ እንዲጥሉ በማድረግ “የአምላክን መንግሥት ቦታ ወሰደች።” ቤተ ክርስቲያኗ፣ ኢየሱስ ተከታዮቹ ‘የዓለም ክፍል መሆን እንደሌለባቸው’ የሰጠውን ግልጽ ትእዛዝ ችላ ብላ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ በመግባት ሥልጣኗን ማጠናከር ጀመረች። (ዮሐንስ 15:19፤ 17:14-16፤ 18:36) ቤተ ክርስቲያኗ የሮም ንጉሠ ነገሥት በነበረው በቆስጠንጢኖስ ተጽዕኖ በመሸነፍ የምታምንባቸውን አንዳንድ ትምህርቶች ቀየረች፤ ከእነዚህ እምነቶች አንዱ የአምላክን ማንነት የሚመለከት ነው።

እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አወዳድር፦ መዝሙር 37:10, 11, 29፤ ዮሐንስ 17:3፤ 2 ጢሞቴዎስ 2:11, 12

እውነታው፦

አብዛኞቹ ጥሩ ሰዎች በሰማይ ሳይሆን በምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ